Fikir Roza

Fikir Roza

Share

God is always good!!

27/01/2026

ንጋት
አየሁኝ ማለዳ..ፀሀይ ስትፈነጥቅ
ከጨለማው ሌሊት..ሳቋ ሲፈለቀቅ፣
ብርሃን ሲወለድ ..ዙሪያ ገባው ሲደምቅ...
አቤት የጮራው ዘርፍ..ይቆማል እንደ ዘንግ..
በቀዝቃዘው አየር..አለም ስትል ፈገግ!!

27/01/2026

ስብዕና
ማን ..ነትህ መስረቱ ሲዋቀር
ከቤተስብ ውርስ የዘር፣
ባህልና ሃይማኖትህ ሆኖ ድምር!
በኖርክበት..የእሳቤ ልክ
ይናገራል ልምምድህ፣
የየቀኑ አካሄድህ፣
ውጤቱ ንህ..ና...
በእርግጥ አንተ የሆንከውን ለመሆንህ!!

27/01/2026

ያች ሴት

በስማሪያ ለማለፍ ..ግድ እንደሆነበት ፍቅር...
ገመናዋን በልቧ ..ይዛ እንደሸሸገችው ምስጢር..
እንስራዋ ለከበዳት ..
ውሃ መቅዳቱ ላደከማት..
ከሀሜትና አሉባልታ..
ከመጣች ሄደች ጥቁምታ..
ለመሸሸግ..ማለዳውን ተኝታ..
በቀትር ፀሀይ ..ዝለት..
መመላለስን ለመረጠች..ለዛች ሴት፣
የህይወትን ውሃ ለመስጠት..
ጌታዋ ተቀምጦ ጠበቃት፣
በስማሪያ ለማለፍ ምክንያቱ እሷ ሆነች
ከዘለአለም ውሃ ጠጥታ..
ለወገኖቾም ተረፈች!!

31/12/2025

እረፍት!
የማወቅ ጅማሮው ሲሆንማ"ከራስ"
ቅድሚያውን ይረዳል..በሚዛን ይሄዳል፤
ጊዜን..ደግሞም ቁስን..እንዲሁም ስሜትን..
መጥኖ ይስጣል..እሱም ይቀበላል፤
የስላም መአዛው መንጭቶ ከራሱ..
ይናኛል ለሌላው ይጋባል መንፈሱ!!

30/12/2025

God is always good!

Category

Telephone

Website

Address

Addis Ababa
Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fikir Roza posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Ababa.