Getahun Milki

Getahun Milki

Share

I am Oromo first

18/07/2026

Dhaamsi kun hawaasa bal'aa bira akka ga'uuf "share" haa goonu.

Beeksisaa Duula Tajaajila Fayyaa Qinda'aa!

03/07/2026

ለጣሊያን ሀገር የሥራ ዕድል የምዝገባ ጥሪ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በገባው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት በህጋዊ የውጪ ሀገር ሥራ ስምሪት ፕሮግራም በጣሊያን ሀገር በሆቴልና መስተንግዶ (Hospitality) ዘርፍ የሰው ኃይል ይፈለጋል።

የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም በማስጠበቅ ህጋዊ በሆነ መንገድ ወደ ጣሊያን ሄደው መስራት የሚፈልጉ አመልካቾች እንዲያመለክቱ እናሳውቃለን።

🏨 የሥራ መደቦች፦

🔹ጸሐፊ(Commis de Rang / F&B Server) – 19 ቦታዎች

🔹 የፅዳት ሰራተኛ (Room Attendant / Housekeeping) – 20 ቦታዎች

🔹 ረዳት ሼፍ (Commis Chef) – 13 ቦታዎች

🔹 የእቃ አጣቢ (Kitchen Steward / Dishwasher) – 11 ቦታዎች

🔹 የወለል ረዳት (Floor Porter / Houseperson) – 3 ቦታዎች

🔹 የቢሮ አስተናጋጅ (Front Office Agent / Receptionist) – 4 ቦታዎች

🔹 የጥገና ቴክኒሺያን (Maintenance Technician) – 1 ቦታ

🔹 የስፓ ቴራፒስት / የማሳጅ ባለሙያ (Spa Therapist / Masseuse) – 1 ቦታ

📌 የማመልከቻ መስፈርቶች

✅ ከስራው ጋር ተያያዥ የስራ ልምድ ያላቸው ተመራጭ ናቸው።

✅ ለአብዛኛዎቹ የስራ መደቦች የእንግሊዝኛ እና/ወይም የጣሊያንኛ ቋንቋ እውቀት ያስፈልጋል።

✅ ለአንዳንድ የሙያ መደቦች ተዛማጅ የሙያ ማረጋገጫ ወይም የሆቴል እና መስተንግዶ ትምህርት ተመራጭ ነው።

📅 የሥራ ቆይታ

አብዛኛዎቹ የስራ መደቦች ለ2026/2027 የክረምት የቱሪዝም ወቅት የሚቀጠሩ ሲሆን፣ አንዳንድ የስራ መደቦች ዓመቱን ሙሉ ወይም በበጋና በክረምት ወቅት የሚሰሩ ናቸው።

✅ ለመመዝገብ

1.Labor ID ካሎት በተሰጠው የማመልከቻ ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ያመልክቱ።

2.Labor ID ከሌሎት የሚከተሉትን ሂደቶች ይከተሉ፦

1. በ lmis.gov.et ይመዝገቡ።
በአቅራቢያዎ ባለ የአንድ ማዕከል (ወረዳ ወይም ቀበሌ) በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ ይስጡ እና የሰራተኛነት መለያ ቁጥር (Labor ID) ይያዙ።

1. Labor ID ካገኙ በኋላ በተሰጠው የማመልከቻ ማስፈንጠሪያ https://forms.lmis.gov.et/italy-hotel/ ገብተው መረጃዎትን በትክክል ሞልተው ያመልክቱ።

ማሳሰቢያ

• ምዝገባም ሆነ ስምሪቲ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ ብቻ የሚከናወን ሲሆን ሚኒስቴሩ ለየትኛውም አካል ውክልናም ሆነ ፈቃድ አለመስጠቱን እንገልፃለን።
• ምንም አይነት ክፍያም የለውም

Category

Telephone

Website

Address

Adama

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Getahun Milki posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Adama.