Dr Getaneh Dejen
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dr Getaneh Dejen, Health/Beauty, Addis Ababa.
Senior Obstetrician & Gynecologist Dedicated to providing exceptional care for women at every stage of life.
📍 Quality Care • Compassionate Service • Trusted Expertis
11/09/2026
ጥሬ ሥጋ እና እርግዝና
በእርግዝና ወቅት ጥሬ ወይም በበቂ ሁኔታ ያልበሰለ ሥጋ መመገብ እንደ ቶክሶፕላዝሞሲስ (Toxoplasmosis) እና ሌሎች ከምግብ ጋር የሚተላለፉ ኢንፌክሽኖችን የመያዝ እድልን ይጨምራል። እነዚህ ኢንፌክሽኖች እናትን ከማሳመም በተጨማሪ በፅንስ ላይም ከባድ ችግር ሊያስከትሉ ይችላሉ።
ስለዚህ ምን ማድረግ አለብዎት?
• ጥሬ ወይም በበቂ ሁኔታ ያልበሰለ ሥጋ አይመገቡ።
• ጥሬ ሥጋ ከነኩ በኋላ እጅዎን በሳሙናና በውሃ በደንብ ይታጠቡ።
• ጥሬ ሥጋ የሚዘጋጅበትን ቢላዋ፣ መቁረጫ ሰሌዳና ሌሎች ዕቃዎችን በደንብ ያጽዱ።
• ጥሬ ሥጋን ከተዘጋጀ ምግብ ለይተው ያስቀምጡ።
• በተለይም የተፈጨ ሥጋ በቂ ሙቀት እንዲያገኝ ያረጋግጡ።
ያስታውሱ፦ በእርግዝና ወቅት በበቂ ሁኔታ ያልበሰለ ሥጋን ያስወግዱ!
መልካም አዲስ አመት
መስከረም 1 2019 ዓ.ም
እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!
REFERRAL SYSTEM IN ETHIOPIA: WHEN A PHONE CALL BECOMES A MATTER OF LIFE AND DEATH
It is deeply disappointing to see how the referral system continues to fail patients in situations where the capacity to provide care actually exists.
Imagine a patient who genuinely needs higher level care. A bed is available in the referral hospital. The necessary specialists and health professionals are available. Yet, despite all these resources being in place, the referring team struggles to get the patient accepted because the liaison or receiving team is not responding.
Even more frustratingly, a physician’s phone number may be provided for communication, only for the phone to remain unanswered for hours, even throughout the entire day. What kind of referral system is this?
This is not simply a communication problem. It is a patient safety problem, a systems problem, and a failure of accountability.
Major referral hospitals carry a critical responsibility in the health system. They should be the strongest link in the referral chain—not the point where the chain breaks.
When referral communication becomes a barrier rather than a bridge, patients may experience unnecessary delays, deterioration, preventable complications, increased costs, and sometimes avoidable deaths.
Let’s talk about our real experiences.
Where does our referral system fail?
Why do referrals get delayed?
Who is accountable when no one responds?
And, most importantly, what practical solutions can we implement?
Because behind every delayed referral is not just a file, a phone call, or a bed request.
There is a patient waiting for care.
29/06/2026
27/06/2026
World PTSD awareness Day
የዓለም ከአሰቃቂ ክስተት በኋላ የሚከሰት የሥነ-አእምሮ ጭንቀት ግንዛቤ ቀን
June 27, 2026
ሰኔ 20, 2018ዓ.ም
PTSD (Post-Traumatic Stress Disorder) ወይም ከአሰቃቂ ክስተት በኋላ የሚከሰት የሥነ-አእምሮ ጭንቀት ማለት፣ አንድ ሰው ከባድና አስፈሪ ክስተት ካጋጠመው ወይም ካየ በኋላ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የሥነ-አእምሮ ችግር ነው።
PTSD ሊከሰት የሚችለው ከምን በኋላ ነው?
👉 በጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት (Gender-Based Violence)፣ የቤት ውስጥ ጥቃት፣ ወሲባዊ ጥቃት እና የሕፃናት ጥቃት
👉ጦርነት፣ ግጭት እና የግዳጅ መፈናቀል
👉የትራፊክ ወይም ሌሎች ከባድ አደጋዎች
👉 የተፈጥሮ አደጋዎች (ድርቅ፣ ጎርፍ፣ መሬት መንቀጥቀጥ)
👉ከባድ የአካል ጉዳት ወይም ሕይወትን የሚያሰጋ ክስተት
በተለይም በጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት (GBV) የPTSD ዋነኛ መንስኤዎች መካከል አንዱ ነው። ብዙ ሴቶችና ልጃገረዶች ከጥቃቱ በኋላ ፍርሃት፣ መረበሽ፣ መጥፎ ሕልም፣ የክስተቱ ተደጋጋሚ ትዝታ እና ሰዎችን ወይም ቦታዎችን መሸሽ የመሳሰሉ የPTSD ምልክቶች ሊያጋጥሟቸው ይችላል።
ስለ PTSD እነዚህን እውነታዎች ልናውቅ ይገባል
👉ይህ ሁኔታ በዕለታዊ ኑሮ፣ በሥራ፣ በትምህርትና በቤተሰብ ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።
👉ከወንዶች ይልቅ ደግሞ ሴቶች ይበልጥ ለዚህ ችግር ተጋላጭ ናቸው።
👉በዓለም ህዝብ ውስጥ በግምት 3.9% የሚሆነው ሰው በሕይወቱ ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ በPTSD ይጠቃል።
👉ከአሰቃቂ ክስተት በኋላ ከቤተሰብ፣ ከጓደኞች ወይም ከሌሎች ሰዎች የሚገኝ የቅርብ ድጋፍ እና ፍቅር በPTSD የመያዝ እድልን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል።
👉 ለPTSD የሚሆኑ ውጤታማና አስተማማኝ ሕክምናዎች ስላሉ ሙሉ በሙሉ ማገገም ይቻላል።
በሀገራችን በኢትዮጵያ ብዙ ሴቶችና ልጃገረዶች እነዚህን ዝምተኛ ሥቃዮች በብቸኝነት እየተሸከሙ ይኖራሉ። ዛሬ ዝምታን እንስበር! በጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃትን በጋራ እንቃወም፤ ተጎጂዎችን በፍቅር፣ በክብርና በርኅራኄ እንደግፍ፤ ለሁሉም ወገኖቻችን የአእምሮ ጤና አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን በቅንጅት እንሥራ።
ጥቃትን እናስቁም፤ የሥነ-አእምሮ ጉዳትን እንረዳ፤ ተጎጂዎችን እንደግፍ!
ዶ/ር ጌታነህ ደጀን ጥጬ
የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሐኪም
https://t.me/getobgyn
31/05/2026
🤰 ጤናማ እርግዝና የሚጀምረው ከማቀድ ነው!
እርግዝና የሕይወት ታላቅ ስጦታ ነው፤ ነገር ግን በእቅድ ሲሆን ለእናትና ለሕፃን የበለጠ ጤናማ ውጤት ያመጣል።
✅ ከመፀነስዎ በፊት የጤና ምርመራ ያድርጉ
✅ ፎሊክ አሲድ መውሰድ ይጀምሩ
✅ የሚኖርብዎትን ህመም (ስኳር፣ ደም ግፊት ወዘተ) ከመፀነስዎ በፊት በተገቢው መልኩ እንዲስተካከል ያድርጉ
✅ ጤናማ ምግብ ይመገቡ
✅ ከአልኮል፣ ሲጋራ እና ሌሎች ጎጂ ልማዶች ይራቁ
ያስታውሱ፦
"የታቀደ እርግዝና ጤናማ እናትና ጤናማ ሕፃን እንዲኖር የመጀመሪያ እርምጃ ነው።"
📌 ይህን መረጃ ለሌሎች እናቶች ያጋሩ!
ይህንን ቻናል ይቀላቀላሉ
ዶ/ር ጌታነህ ደጀን(የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሐኪም ) / Dr.Getaneh Dejen(Assistant Professor of Obstetrics and Gynecology) የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ✅የቅድመ እርግዝና, የእርግዝ የድህረ ወሊድ ክትትልና እና ህክምና ✅ከወርአበባ ጋር ተያያዥ ችግሮች ህክምና ✅የመካንነት መርመራ እና ህክምና ✅የካንሰር ምር...
31/05/2026
ከቀን በፊት ምጥ መምጣት
Preterm Labor
አንድ ነፍሰ ጡር ሴት መደበኛ የእርግዝና ጊዜዋን (37 ሳምንታት) ሳታጠናቅቅ፣ ከ28ኛው እስከ 37ኛው ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ የምጥ ምልክቶች ካሳየች ይህ "ከቀን በፊት የመጣ ምጥ" ይባላል። ይህ ምጥ ወደ መውለድ ከተቀየረ ደግሞ "ያለቀኑ መውለድ(preterm birth)" ተብሎ ይጠራል።
ሀ. ያለቀኑ ምጥ/መውለድ ለምን ይከሰታል?
ያለቀኑ መውለድ/ምጥ ትክክለኛ መንስኤ ሁልጊዜ በትክክል ባይታወቅም፣ በህክምና ሳይንስ የተረጋገጡ ዋና ዋና ተጋላጭነቶችና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦
1. ኢንፌክሽኖች
👉የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
👉የብልት እና የማህፀን ኢንፌክሽኖች
👉ከፍተኛ ትኩሳት የሚያስከትሉ ህመሞች
2. የእናት የጤና ችግሮች
👉ከፍተኛ የደም ግፊት
👉የስኳር በሽታ
👉ከፍተኛ የደም ማነስ
3. የእርግዝና ችግሮች
👉መንታ ወይም ከዚያ በላይ ፅንስ
👉የእንሽርት ውሃ ቀድሞ መፍሰስ
👉የማህፀን ወይም የማህፀን ጫፍ ችግር
4. የአኗኗር ሁኔታዎች
👉ሲጋራ ማጨስ
👉አልኮል መጠጣት
👉አደንዛዥ እፅ መጠቀም
5. ቀደም ሲል ያለጊዜው ወሊድ መኖር
👉በፊት ቅድመ ጊዜ ወሊድ ያደረጉ እናቶች እንደገና የመደገም አደጋ ከፍ ያለ ነው።
ለ. ያለቀኑ ምጥ ምልክቶች ምንድናቸው?
እነዚህ ምልክቶች ከታዩ በአስቸኳይ ወደ ጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል። ምጥ ከቀኑ ቀድሞ ከጀመረ ህክምና በማግኘት እንዲቆም ወይም ህጻኑ እንዲጠነክር ማድረግ ይቻላል።
✅ በ10 ደቂቃ ውስጥ ከ1 ጊዜ በላይ የሚደጋገም የማህፀን መኮማተር (ምጥ)
✅ የወገብ ህመም ወይም የታችኛው ጀርባ ህመም
✅ የወር አበባ ህመም የሚመስል የሆድ ቁርጠት
✅ በዳሌ አካባቢ ከባድነት ወይም ግፊት መሰማት
✅ ከብልት የሚወጣ ፈሳሽ መጨመር
✅ የእንሽርት ውሃ መፍሰስ
✅ ከብልት ደም መታየት
ሐ. ያለጊዜው ምጥን እና ወሊድን ለመከላከል ምን ማድረግ ይቻላል?
1. ቀድሞ እና መደበኛ የእርግዝና ክትትል (ANC) ማድረግ፡
👉የጤና ችግሮች ቀድመው እንዲታወቁ ይረዳል።
2. ኢንፌክሽኖችን በጊዜው ማከም፡
👉የሽንት ህመም፣ መቃጠል ወይም የብልት ፈሳሽ ለውጥ ካለ ወዲያውኑ ሕክምና መፈለግ።
3. ጤናማ አመጋገብ፡
👉ብረት፣ ፎሊክ አሲድ፣ ፕሮቲን እና አትክልት/ፍራፍሬ በበቂ መጠን መመገብ።
4. ሲጋራ፣ አልኮል እና አደንዛዥ እፅን መቆጠብ
5. የእናት ህመሞችን መቆጣጠር:
👉የደም ግፊት፣ የስኳር በሽታ እና ሌሎች ህመሞችን በሐኪም ምክር መከታተል።
6. አጭር የማህፀን ጫፍ (Short Cervix) ካለ ቀደም ሲል ቅድመ ጊዜ ወሊድ ካለ በእነዚህ ሁኔታዎች ሐኪሙ የፕሮጀስትሮን ሕክምና ወይም የማህፀን ጫፍ ስፌት (Cerclage) ሊመክር ይችላል።
📌ማሳሰቢያ: መደበኛ የእርግዝና ክትትል ማድረግ፣ ኢንፌክሽኖችን በጊዜው ማከም እና የምጥ ምልክቶችን ማወቅ የእናትና የሕፃን ሕይወት ለማዳን ይረዳል። ማንኛውም ከላይ የተጠቀሱት የምጥ ምልክቶች ሲታዩ፣ በተለይ የእርግዝና ሳምንት ከ 37 በታች ከሆነ፣ በቤት ውስጥ ለመጠበቅ ሳይሞክሩ በአስቸኳይ ወደ ቅርብ ሆስፒታል ወይም የጤና ጣቢያ መሄድ ለእናቷም ሆነ ለጽንሱ ህይወት ወሳኝ ነው።
በዶ/ር ጌታነህ ደጀን
የማህፀንና የጽንስ ሕክምና ስፔሻሊስት
ዶ/ር ጌታነህ ደጀን(የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሐኪም ) / Dr.Getaneh Dejen(Assistant Professor of Obstetrics and Gynecology) የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ✅የቅድመ እርግዝና, የእርግዝ የድህረ ወሊድ ክትትልና እና ህክምና ✅ከወርአበባ ጋር ተያያዥ ችግሮች ህክምና ✅የመካንነት መርመራ እና ህክምና ✅የካንሰር ምር...
30/05/2026
የአዕምሮ ጤናግንዛቤ ወር
ከወሊድ በኋላ የሚከሰተውን የአዕምሮ ጤና ሁኔታ (Postpartum Mental Health)
ብዙ ጊዜ አዲስ ህጻን ሲወለድ ደስታ ብቻ የሚኖር ቢመስልም፣ ለብዙ እናቶች ግን ከባድ የሆርሞን፣ የባህሪ እና የስሜት መዋዠቅ የሚያስተናግዱበት ወቅት ነው።
ከወለዱ በኋላ ባሉት 2-3 ቀናት ውስጥ የሚጀምር፣ ማልቀስ፣ መበሳጨት እና ጭንቀት የሚታይበት ሁኔታ እናቶች ላይ የሚከሰት ሲሆን፣ እነዚህ ምልክቶች ያለ ምንም ህክምና ከሁለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በራሱ ይጠፋል።
ነገር ግን በጣም የጠነከረ እና ከሁለት ሳምንት በላይ የሚቆይ የድብርት ስሜት ፣ እናትየው ከልጇ ጋር የመቀራረብ ስሜት ሲጠፋት፣ ከፍተኛ የተስፋ መቁረጥ፣ የማያቋርጥ ድካም እና ራሷን ወይም ህጻኑን የመጉዳት ሃሳብ ሊመጣባት ይችላል። ይህም ወሊድ በኋላ ድብርት ሲሆን የህክምና እርዳታ ይፈልጋል።
በመሆኑም አንዲት አዲስ እናት የሚከተሉት ምልክቶች ከሁለት ሳምንት በላይ ከቆዩባት ትኩረት ያስፈልጋታል፦
• ያለቅልቁ ከባድ ሀዘን እና በተደጋጋሚ ማልቀስ
• ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ራስን ማግለል
• ከልጁ ጋር ፍቅር ለመመስረት መቸገር ወይም ፍርሃት መሰማት
• ከመጠን በላይ መተኛት ወይም ጨርሶ እንቅልፍ ማጣት
• እኔ ጥሩ እናት አይደለሁም የሚል ከባድ የጥፋተኝነት ስሜት
ምን ማድረግ ይገባል?
ስሜትን በግልፅ መናገር: የሚሰማዎትን ከባድ ስሜት፣ ፍርሃትና ጭንቀት ለትዳር አጋርዎ፣ ለቅርብ ጓደኛዎ ወይም ለቤተሰብዎ በግልፅ ያካፍሉ።
ልጅን ለመንከባከብ፣ ምግብ ለማብሰል ወይም የቤት ውስጥ ስራዎችን ለመስራት የቅርብ ሰዎች እገዛ በማግኘት እረፍትና በቂ እንቅልፍ ያስፈልጋታል።
ስሜቱ እየበረታና የዕለት ተዕለት ህይወትን እየጎዳ ከመጣ፣ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ከጤና ባለሙያ የህክምና እገዛ ማግኘት ያስፈልጋል።
ለቤተሰብ ማስታወሻ፦ የወሊድ በኋላ ድብርት የእናትየው ድክመት ወይም ስንፍና ሳይሆን የጤና እክል ነው። በዚህ ወቅት እናቶች ፍቅር፣ እንክብካቤ እና ከፍርድ ነፃ የሆነ ድጋፍ እንጂ ወቀሳ አያስፈልጋቸውም።
ዶ/ር ጌታነህ ደጀን(የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሐኪም ) / Dr.Getaneh Dejen(Assistant Professor of Obstetrics and Gynecology) የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ✅የቅድመ እርግዝና, የእርግዝ የድህረ ወሊድ ክትትልና እና ህክምና ✅ከወርአበባ ጋር ተያያዥ ችግሮች ህክምና ✅የመካንነት መርመራ እና ህክምና ✅የካንሰር ምር...
EID MUBARAK
ዒድ ሙባረክ !
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን 1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ)በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
25/05/2026
World Thyroid Day
ግንቦት 17, 2018 ዓ.ም
May 25, 2026
እንኳን ለዓለም አቀፍ የታይሮይድ ቀን (World Thyroid Day) በሰላም አደረሳችሁ! ይህ ቀን ስለ ታይሮይድ እጢ ጤንነትና መታወኮች ግንዛቤ የሚፈጠርበት ሲሆን፣ በተለይም በእርግዝና ወቅት የታይሮይድ ሆርሞን መዛባት በእናትና በጽንስ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ስለሚያሳድር ልዩ ትኩረት ይሻል።
ታይሮይድ (Thyroid ) እና እርግዝና
የታይሮይድ እጢ በአንገታችን የፊት ለፊት ክፍል ላይ የሚገኝ የቢራቢሮ ቅርጽ ያለው ትንሽ እጢ ሲሆን ይህ እጢ የሰውነታችንን የስነ-ህይወታዊ እንቅስቃሴ (Metabolism) የሚቆጣጠሩ ሆርሞኖችን ያመርታል።
በእርግዝና ወቅት የጽንሱ አጠቃላይ የጭንቅላትና የሰውነት እድገት በመጀመሪያዎቹ 12 ሳምንታት (የመጀመሪያው ሶስት ወር) ሙሉ በሙሉ በእናትየው የታይሮይድ ሆርሞን ላይ የተመሰረተ ነው። ስለዚህ በእናትየው ላይ የሚኖር የሆርሞን መዛባት በቀጥታ ልጁን ይነካል።
ዋና ዋናዎቹ የታይሮይድ እጢ መዛባቶች
በእርግዝና ወቅት ሁለት ዋና ዋና የሆርሞን መዛባቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፦
1. የታይሮይድ ሆርሞን ማነስ (Hypothyroidism)
ይህ የሚከሰተው የታይሮይድ እጢ በቂ ሆርሞን ማምረት ሲያቅተው ወይም በሰውነታችን ውስጥ የሆርሞን እጥረት ሲኖር ነው።
ምልክቶቹ፦
• ያለበቂ ምክንያት የሰውነት ክብደት መጨመር
• በቀላሉ ብርድ ብርድ ማለት
• የቆዳ መድረቅ
• የሆድ ድርቀት
• የድብርት ወይም የቅያሜ (የስሜት መውረድ) ስሜት
• የልብ ምት መዘግየት
• የፊት እብጠት
• የድምፅ መጎርነን
(እነዚህ ምልክቶች ከተለመደው የእርግዝና ድካም ጋር ሊመሳሰሉ ስለሚችሉ በምርመራ መለየት ያሻል)።
ሊያስከትለው የሚችለው አደጋ፦ በአግባቡ ካልታከመ ውርጃ (Miscarriage)፣ ያለቀን መውለድ፣ የደም ግፊት (Preeclampsia) እና በልጁ የአእምሮ እድገት ላይ ተፅዕኖ ሊያደርስ ይችላል።
2. የታይሮይድ ሆርሞን መብዛት (Hyperthyroidism)
ይህ ደግሞ እጢው ከተገቢው በላይ በከፍተኛ መጠን ሆርሞን ሲያመርት የሚከሰት ነው።
ምልክቶቹ
• ያለበቂ ምክንያት የሰውነት ክብደት መቀነስ
• ፈጣን ወይም መደበኛ ያልሆነ የልብ ምት
• የመረበሽ ወይም በቀላሉ የመበሳጨት ስሜት
• ከፍተኛ የላብ መውጣት
• የእጅ መንቀጥቀጥ
• የእንቅልፍ እጦት ወይም ለመተኛት መቸገር
• ሙቀትን መቋቋም አለመቻል
ሊያስከትለው የሚችለው አደጋ፦ የፅንስ እድገት መገታት፣ ያለቀን መውለድ እና በእናትየው ላይ ከፍተኛ የልብ ህመም ማምጣት።
ማሳሰቢያ :
ምልክቱ የሚታይባቸው ነፍሰ ጡር እናቶች ወደ ጤና ተቋም በመሔድ መመርመርና ህክምናን ሳያቋርጡ መከታተል አስፈላጊ ነው። የታይሮይድ መዛባት በደም ምርመራ በቀላሉ የሚታወቅና ደህንነቱ በተጠበቀ ክኒን መታከም የሚችል ህመም ነው።
ዶ/ር ጌታነህ ደጀን ጥጬ
የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሐኪም
የህክምና እና የምክር አገልግሎት ለማግኘት
📱 0913292030
📝
አድራሻ
🏥 ደብረ ብርሃን ዩንቨርስቲ ሀኪም ግዛው ሆስፒታል
🏥አዲስ ብርሃን ስፔሻላይዝድ ህክምና ማዕከል
📌 ሼል ነዳጅ ማድያ አጠገብ,
ደብረ ብርሃን
Category
Telephone
Website
Address
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when Dr Getaneh Dejen posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.
