Zeheabsha

Zeheabsha

Share

beauty and health

Photos from Zeheabsha's post 07/12/2023
07/12/2023

ይህንን ነው መፍራት..........

26/05/2023

70 ዓመት ዳቦ ያበሉን የ'ሸዋ ዳቦ' መሥራች አቶ ዘሙይ ተክሉ አርፉ ።
*******************************************************
በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች " ሸዋ ዳቦ መጋገሪያ " የሚል መጠሪያ ያለው ዳቦ ቤት መሥራች አቶ ዘሙይ ተክሉ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ታውቋል።

ነፍስ ይማር ።

23/05/2023

ማታ ማታ ባል ያምረኛል ።

ከአበባ ብርሃኑ

አበባ ይዞ ከስራ የሚመለስ፣ ሲገባ ደግሞ ብሔሬን እስክረሳ ድረስ የሚስመኝ ፣ አንገቴን ስሞ ትንፋሼን የሚያዳምጥ፣ የልብ ምቴን አስተካክሎ ሲጨርስ አዋዋሌን የሚጠይቀኝ ፣ ራት ሳቀራርብ የሚያግዘኝ ፣ የመጀመሪያውን ጉርሻ ለኔ የሚያጎርሰኝ፣ አንዴ ጎርሶ ሙያየን የሚያደንቅልኝ ፣ ከራት በሁዋላ ዋይን ቀድቶ የሚያቀብለኝ፣ አጠገቤ ሆኖ እየዳበሰ ውሎውን የሚተርክልኝ -- የሚያማክረኝ ምናምን ----

ይህን ሁሉ ፍለጋ ፍቅር የሚያውቅ ሰው አገባሁ ።

ባገባሁት በነጋታው ፍቅረኛ መሆኑ ቀርቶ አባዎራ ሆነ ።

ውሎ ሲያድር ማታ ማታ
'የት ነህ?' እያልኩ ሶስት ጊዜ መደወል ጀመርኩ፣ ስልኩ ስለማይነሳ
'ደንበኛችን ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ናቸው-- ' ከምትለው ሴት ጋር ዝምድና ፈጠርን ። -'ደህና ነሽ ?' 'አስቸገርኩሽ እንግዲህ ' ምናምን እላት ጀመር።

እሷም ተጨንቃ
' ምን ታረጊዋለሽ አብዛኛው ባሎች እንዲህ ናቸው ' ብላኝ ታውቃለች።

አመሻሽቶ ሲገባ የአበባ ሽታ ሳይሆን ቢራ ቢራ እያለ መግባት ጀመረ በእጁም ኮቱን አንጠልጥሎ ስለሚገባ በእጅም ሳንነካካ እንቀራለን።

ሲገባ አያየኝም ፣ ሻሽ ልሰር ወይ አናቴ ላይ ድመታችንን ልሸከም አያይም ።

እራት ሳቀርብ ቲቪ ይከፍታል :---
ሳቀርብ ሳያየኝ ይጎርሳል ' ባለሙያ' በሚል ሙገሳ ፋንታ 'እስኪ ወጥ ነገሩን ጨምሪበት ' ይለኛል።

በልቶ ሲነሳ ማፅዳት እቀጥላለሁ እሱ ቲቪ ማየት ይቀጥላል ፣ ኳስ ከፍቶ ይመሰጣል 'ዋው ' እያለ ግብ ያደንቃል። አንዲት ድብልብል ጉድ ከኔ መብለጥዋ ያናድደኛል ---

ቢቸግረኝ የባልን አትኩሮት መሳቢያ ስድስት ሺህ መንገዶች የሚለውን መፅሃፍ ገዝቼ አንብቤ

ራሴን አሳምሬ ፣ ስስ ፒጃማ ለብሼ: እንዲያየኝ ፊት ለፊቱ መወዝወዝ ጀመርኩ። አትኩሮት ለመሳብ ነበር -- እሱ እቴ

'እስኪ ቲቪውን አትከልይኝ ' ብሎኝ ቁጭ።

አትኩሮት ለመሳብ የማደርገው ሁሉ አተካሮ ያስነሳብን ጀመር።

ልንተኛ ስንል ትራሱን ያቅፋል ፣ ስነካው ያንኮራፋል ፣ ያ ነገር ላይማ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀበት ይመስላል
--- አለ አይደል ወዲያው ተሳፍሮ ቅርብ ይወርዳል ፣

በቃ:- አልጠራሁም እንጂ ወያላ በሉኝ :-
በር ከፍቶ ማስገባት እና ማውረድ ነገር።

ሁለት ሜትር አልጋችን ምንም ካልተጠቀምንበት የቤት ዕቃችን መሃል አንዱ ሆነ።

አብረን ከወጣን አለባበሴን የሚያደንቀው ሰውየ አሁን እራቁን ልውጣ ልልበስ ፣ ቦርሳ ልያዝ የቤታችንን ቡችላ ልዘል አያይም።

ወር ሲደርስ እንደ ኦዲተር አብረን ወጪ እና ገቢ መደመር ሆነ ስራችን ።

ሲመስለኝ ባለቤቴ ድሮ ሳንጋባ የነበረውን ፍቅሩን ሰርጋችን ላይ 'ሎጋሽቦ ' ሲጨፍር እና ሲዘልል ሳይጥለው አይቀርምና ሲወድቅበት ያየ ወይም የወደቀበትን የሚያውቅ ቢያሳውቀኝ ወሮታ ከፋይ ነኝ።》

24/03/2023

የስራው አይነት - ብብት ማሽተት

ደሞዝ - ከ74,000 እስከ 110,000 ዶላር በአመት

አለም ላይ አሉ ከሚባሉ አስገራሚ/weird ስራዎች አንዱ ነው - ብብት የማሽተት ስራ ! ደሞዙ ደግሞ ከከፍተኛ ተከፋይ ስራዎች ተርታ የሚመደብ ነው

ይህንን ስራ የሚቀጥሩት የዶዶራንት እና የብብት ሽታ ማጥፊያ ሽቶዎችን/ስፕሬይ በሚቀምሙ ድርጅቶች ነው:: ድርጅቶቹ የቀመሙትን ዶዶራንት ወይም ሽቶ ሰው ብብት ላይ ነፍተው ሰውዬው ለተወሰኑ ቀናቶች ገላውን ሳይታጠብ ይከርማል - ከዚያው የጠረኑን ለውጥ እያሸተቱ ለባለሞያው መንገር ነው🤗

አልያም ደግሞ ሰውዬው መጀመርያ ሳይታጠብ ይቆያል ከዚያም ብብት አሽታቹ አሽትቶ የሽታውን መጠን በደረጃ ያስቀምጣል:: ከዚያም ደግሞ ሰውዬው ዶዶራንቱን ወይም ሽቶውን ይቀባል -ብብት አሽታቹ በድጋሚ ያሸታል - ከዚያም ሰውዬው ከነሽታው ይቆይና በድጋሚ ይሸተታል🤗🙄

ይህ ብብት ማሽተት በእድሜ: በጾታ :በቆዳ ቀለም: ደንበኞች በሚመገቡት የምግብ አይነት እና በተለያዩ መመዘኛዎች ተከፋፍሎ የሚደረግ ሲሆን ብብት አሽታች ለመሆን ምንም አይነት የትምህርት ደረጃ አልያም የስራ ልምድ አይጠየቅበትም ይባላል

ለማንኛውም
የምትቀቡት ዶዶራንት እና የብብት ስፕሬይ/ሽቶ ይህንን ሁሉ ሂደት አልፎ ነው🤗
በዘመላክ እንድሪያስ

Photos from Zeheabsha's post 09/03/2023

ከነገ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ታገደ

| በአዲስ አበባ ከተማ ከነገ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የባለ ሦስት እና አራት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎችን ማሽከርከር እንደማይቻል የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ከቢሮው ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው÷ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን በተሻለ መልክ ለመምራት የሚያስችል የአሰራር ማሻሻያ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡

በመሆኑም የአሰራር ማሻሻያው ተጠናቆ እና የአገልግሎቱ አስፈላጊነት በዝርዝር ተጠንቶ ውሳኔ እስከሚያገኝ ድረስ÷ ከነገ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አካባቢ ላልተወሰነ ጊዜ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የታገደ መሆኑን ነው ቢሮው የገለጸው፡፡

20/02/2023

እውነትም ስታገባ ይገባሀል

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Addis Ababa
KARULOVE123