Feben liben
እንታረቅ
29/01/2025
ራሱን የጽንፈኛ ቡድን መሪ አድርጎ የሚቆጥረው መሪ ተደመሰሰ!!
በደቡብ ወሎ ዞን ጥምር ጦሩ በወሰደው እርምጃ ከአምሀራ ሳይንት እስከ ለጋምቦ ህዝብን ሲዘርፍና ሲያገላታ የነበረው የጽንፈኛ ቡድኑ መሪ ሃ/አለቃ ጌታቸር ተሾመ ከአራት ግብረ አበሮቹ ጋር እስከ መጨረሻው ተሸኝቷል።
በተጨማሪም በዛሬው እለት በቃሉ ወረዳና በሀርቡ ከተማ መገናኛ ቦታ ላይ ከሰሜን ሽዋ ዞን ወደ ሰሜን ወሎ ዞን ጽንፈኛ ኃይሉ ስናይፐር ይዞ ሲቀሳቀስ በቁጥጥር ስር ውሏል።
በተመሳሳይ በተሁለደሬ ወረዳ የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ሀያ ስድስት የጽንፈኛ ኃይሉ አባላት ለጥምር ጦሩ እጅ ሰጥተዋል።
በዞኑ በጥምር ጦሩ አማካኝነት በሁሉም አቅጣጫዎች ውጤታማ ህግ የማስከበር ጉዞ በድል በመታጀብ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።
30/11/2024
ሰበር የድል ዜና !!
በደቡብ ወሎ በወግዲ፤ በቦረና፤ በአምሀራ እና መሀል ሳይንት፤ በደላንታ እና በአምባሰል በተደረገው የተቀናጀ ጥላትን የማጥፋት እርምጃ በርካታ ጽንፈኛ ኃይሉ ሙት እና ቁስለኛ ሲሆኑ አብዛኛው እጅ እየሰጠ ሲሆን የቡድን መሳሪያ ጭምር ተማርኳል።
«ደውላችሁ ጠይቁ» በደላንታ ፀሀይ መውጫ የጽንፈኛ ኃይሉ ከፍተኛ አመራር ላይመለስ እስከወዲያኛው ተሰናብቷል።
16/09/2024
በእብሪት የተንጠራሩትን አንበርክኮ የሰላም ያለህ የሚያስብለው ሰራዊት የመጨረሻ ተልዕኮ መሰጠቱ ተሰምቷል
በኢትዮጵያ አድማስ ውስጥ ሰላምን በማደፍረስ ለጠላት ስውር ፈረስነት የተሰለፉ እንቅፋቶችን ከዚህ በላይ እንደማይታገስ መንግስት ማስታወቁን የውስጥ መረጃዎች አስታውቀዋል።
መንግስት መደናገር የተፈጠረባቸውን አካላት ለማትረፍ በዝምታ ቢመለከትም ከዚህ በኋላ ለፅንፈኛ ምህረት የለኝም ለጠታቶቼ ስውር እጆችም በሀገሬ አይወራጩም ማለቱ ነው የተሰማው።
ሰላምን አሜን ብሎ ለማይቀበል የጦስ ዶሮ አዘኔታ የለንም።በፅንፈኞች ጥፋት የማይገባ መከራ ተቀብለናል።
27/08/2024
በክልሉ በተከሰተው ወቅታዊ የተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ኮሚሽኑ ገለጸ።
ከፍተኛ እና የተራዘመ የዝናብ መጠን ያለበት የክረምት ወቅት በመሆኑ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጥሮ አደጋዎች እንደተከሰቱ የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ገልጿል።
የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋሁን ባታብል በክልሉ ወቅታዊ የተፈጥሮ አደጋ እና እየተሰጠ ባለው ምላሽ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ኮሚሽኑ በክልሉ ዝናቡ ከበደ እያለ በመምጣቱ ጎርፍ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ፣ የመሬት መንሸራተትና መሰል አደጋዎች እየተከሰቱ መሆኑን አስታውቋል።
በብሔራዊ ሚትዮሮሎጂ 4መቶ ሺህ የሚጠጉና ከ28ሺህ በላይ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በተፈጥሮ አደጋ ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ የቅድመ ትንበያ ስራ ተሰርቶ ከበጋ ጀምሮ ዝግጅት መደረጉን የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋሁን ባታብል ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የቅድመ ትንበያውን መነሻ በማድረግ በበጋው በርካታ የአደጋ መከላከል ሥራዎች ቢሠሩም ከፍተኛ የዝናብ መጠን በመኖሩና በክረምቱ መክበድ ምክንያት በሰሜን ጎንደር፣ በደቡብ ጎንደር እና በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ ክስተቶች መኖራቸውን ኮሚሽነሩ አንስተዋል።
የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋሁን ባታብል በሰሜን ጎንደር ጠለምት ወረዳ የተከሰተው የመሬት መንሸራተት 10 ሰዎችን ለሞት ሲዳረግ 2ሺህ 9መቶ 49 የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመፈናቀል እንደዳረገም ገልጸዋል።
በክልሉ 45ሺህ ኩንታል ለቅጽበታዊ ችግሮች መጠባበቂያ የሰብአዊ ድጋፍ መኖሩን ያስታወሱት ኮሚሽነሩ በሰሜን ጎንደር ጠለምት ወረዳ ለችግር ለተጋለጡት ወገኖች የእለት ምግብ እየቀረበ መሆኑን ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።
በመጨረሻም መንግስታዊና እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማስተባበር በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸውና ለተፈናቃሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እንዲደርስ ኮሚሽኑ እየሰራ ሲሆን ክረምቱ እስከ መስከረም አጋማሽ ድረስ ተጠናክሮ ሊቀጥል ስለሚችል ህብረተሰቡ የተለያዩ የተፈጥሮ አደጋዎች ምልክት ባየ ጊዜም ከአካባቢው ርቆ በመቆየት የአደጋውን ጉዳት እንዲቀንስ የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋሁን ባታብል ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
•~•~•
"የጣና ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
26/08/2024
‹‹የትምህርት ለትውልድ›› ስራችን የሁሉንም ተሳትፎ የሚፈልግ እና የችግራችንን ሰንኮፍ ከመሰረቱ የመፍቻ ቁልፍ ነው !
ትምህርት የመልካም ስነ-ምግባር ባለቤት ፣ የምክንያታዊነት እና ግብረ ገብነት ፤ የተወዳዳሪነት እና ተባባሪነት ፣ የችግር ፈቺነት እና መፍትሔ አፍላቂነት ብቃት ያላቸው ዜጎች መቅረጫ መሳሪያ ነው፡፡ የአዳዲስ እይታዎች ምንጭ ፣ የሁለንተናዊ ህብረተሰባዊ ለውጥና ብልፅግናም ሞተር ነው፡፡
በክልላችን ህዝብ ዘንድም ትምህርትና እውቀት ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ እንደ ሀገር ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት ካለው የአጠቃላይ ትምህርት ማሻሻያ እንቅስቃሴ ባሻገር ለኛ ክልል ደግሞ በዚህ ዓመትና በቀጣይ ጊዜያት የምንሰራቸው ስራዎች ልዩ ትርጉም የሚሰጣቸው ናቸው፡፡
የትምህርት ዘመኑ ተልዕኳችንን ጥብቅና የሁላችንንም ቁጭት የተሞላ ትብብር አስፈላጊ የሚያደርጉ ምክንያቶችም አሉ፡፡
የክልላችን መንግስት የዘርፉን ችግሮች እና አቅሞች በመለየት ‘‘የትምህርት ለትውልድ’’ ንቅናቄ በማካሄድ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ማስተባበር ላይ የተመሰረቱ በርካታ ተግባራትን በክረምቱ ሲያከናውን ቆይቷል፡፡
ባለፈው የትምህርት ዘመን በክልላችን ባጋጠመው የሰላም እጦት የተነሳ መማር ካለባቸው ህፃናትና ወጣቶች በርካቶች ከትምህርት ገበታ ውጭ ያደረገ ሲሆን በርካታ ወደኋላ መላሽ ችግሮች አስተናግደናል፡፡
የዚህ የትምህር ዘመን ስራችን በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ያለፉንን እድሎች በቁጭት የሚያካክስ እና መሰረታዊ የሚባል ለውጥ በማድረግ ትውልዱን የሚታደግ መሆን ይኖርበታል፡፡
አሁን የተጀመረው የተማሪዎች ምዝገባንም ጨምሮ በእያንዳንዱ ምዕራፍ ልዩ ትኩረታችንን እና የሁላችንን መተባበር ይፈልጋሉ፡፡ማናቸውም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናትና ወጣቶችን ወደ ትምህርት ምዝገባ ከማምጣት ጀምሮ የትምህርት ተቋማትን ገፅታን በማሻሻል እንዲሁም ለመማር ማስተማር ስራው ምቹ በማድረግ የህብረተሰባችን ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ አጠናክሮ እንዲቀጥል ይጠበቃል።
በትምህርት ላይ የምንሰራቸው የብቁና ንቁ፣ የምግባረ መልካምና ተወዳዳሪ ትውልድ ፈጠራ ስራችንን ማሳካት በዘላቂነት የችግሮቻችንን ሰንኮፍ ነቃይና ፀጋዎቻችን አስተባብሮ ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና አሻጋሪ መሰረትን የማኖር ጉዳይም ጭምር ነው።
ያለፈው ስህተት እንዳይደገም እንማርበታለን እንጂ ተቀምጠን አንቆዝምበትም። የዛሬያችንን እድል በትብብር አሟጠን ለትውልዱ መልካም ሰርተንበት የነጋችንን መሰረት እናሳምር።
🕊ሠላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
•~•~•
"የጣና ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
26/08/2024
ትምህርት ለሀገር ዕድገት ብልጽግና ወደር የማይገኝለት ተግባር ነዉ!!!
የ2017ዓ.ም የትምህር ዘመን ምዘገባ ተጀምሯል! እኛም ልጆቻችንን አስመዝግበን ወደ ትምህርት ገበታቸዉ እንመልስ!
!
20/08/2024
"የበጎ ፈቃድ ስራ የህሌና እርካታ የሚከፈለው ሲሆን ይህ ተግባር የመንግስት የበጀት ጉድለቶችን በመሙላት የዜጎችን ኑሮ ምቹ ለማድረግ የሚሠራ ነው"
!
16/08/2024
!
ገበያ ላይ ነን!!!
12/08/2024
የግብርና ሜካናይዜሽን ለውጤታማ ምርታማነት!!
!
Click here to claim your Sponsored Listing.
