Saro Tube
እዉነት የደስታ ምንጭ ነች። 🇩🇪🇩🇪🇩🇪
ዮ ዮ ዮ ማስቃላ በጋሞ ዞን በቁቁጫ ወረዳ በሦስቱ መዋቅር
10/08/2026
የፏፏቴው ድምፅ ከሩቅ ይሰማል፤ ውሃው ከከፍታ ላይ በኃይል እየተወረወረ በድንጋዮች ላይ ይፈሳል። የውሃው ጠብታዎች በፀሐይ ብርሃን ሲንፀባረቁ እንደ ብር ዕንቁዎች ያበራሉ፤ ድንቅ ስፈፍራ ነው።
"ቱርሞ ፏፏቴና ዋሻ"
ይህ አስደናቂ መንቲያ ፏፏቴና ዋሻ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ በቶባ ጹሎ ቀበሌ ይገኛል።
ከመንቲያው ፏፏቴ ስር ያለው ዋሻም ለፏፏቴው ልዩ ውበት ጨምሯል የዋሻው ግድግዳዎች በዘመናት በተፈጥሮ የተቀረጹ ይመስላሉ። ወደ ዋሻው ውስጥ ሲገባ ቀዝቃዛ አየር መንፈስን ያድሳል፤ የውሃ ጠብታዎችም ዋሻውን እየታከኩ ከጣሪያው በፍጥነት ይወርዳሉ ይህ ሁሉ ለጎብኚዎች ልዩ የሆነ የደስታና የሰላም ስሜት ይፈጥራል።
ውሃው በድንጋዮች ላይ እየተመታ ነጭ አረፋ ይፈጥራል፤ የሚበተነውም የውሃ ጭጋግ አካባቢውን በቀዝቃዛ እርጥበት ይሞላዋል።
የቱርሞ ፏፏቴው፣ ዋሻው፣ ውሃውና አረንጓዴው መልክዓ ምድር ተዋህደው የፈጠሩት አስደናቂ የተፈጥሮ ስፍራ ነው።
የቱርሞ መንቲያ ፏፏቴና ዋሻ በአረንጓዴ ዛፎችና በለመለመ ሣር መካከል መሆኑ ውበቱን ይበልጥ አጉልቶታል
በእውነት የቱርሞ ፏፏቴ እና ዋሻ ውበት በቃላት ብቻ ሊገለጽ አይችልም። ሲፈስ፣ ሲያብረቀርቅና በድንጋይ ላይ ሲደርስ የሚፈጥረው ድምፅ ልብን ይሰርቃል።
የቱርሞን ፏፏቴና ዋሻን ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም፣ የ"ሳሮ ሃይኪንግ" መስራች ደራርቱ ባንቲ እና የጎፋ ቴሌቪዥን የሚዲያ ቡድን አባላት የጎበኙ ሲሆን በጉብኝቱ የመሎ ኮዛ ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽመልስ ገዛኸኝ ለጎብኝዎች ስለ ወረዳው አጠቃላይ የቱሪዝም ሀብትና ፀጋዎች እንዲሁም ስለ ቱርሞ ፏፏቴና ዋሻ ገለጻ በማድረግ አካባቢውን ለቱሪስት ምቹ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
04/08/2026
የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ግዙፍ ፕሮጀክት ነው - ሲኤንኤን
መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው ሲኤንኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት በአፍሪካ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ግዙፍ ፕሮጀከት ነው አለ፡፡
በሲኤንኤን የኬንያ ተወካይ ዘጋቢ የሆነችው ቪክቶሪያ ሩባደሪ ባሰናዳችው ዘገባ÷ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካውያንን ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በማገናኘት እጅግ ስኬታማው አየር መንገድ መሆኑን ገልጻለች፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራሱን ይበልጥ ለማሳደግና ተደራሽነቱን ለማስፋት የቢሾፍቱ አየር መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን ይፋ ማድረጉን በማንሳት፤ የአየር መንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ በአፍሪካ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑን አብራርታለች፡፡
ነገሮች በታቀዱት መንገድ የሚሄዱ ከሆነ በ2030 የአየር መንገዱ ግንባታ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ጠቅሳለች፡፡
የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ከ12 ቢሊየን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ ሲሆን የኢትዮጵያን አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን የሚደግፍ መሆኑንም በዘገባዋ አመልክታለች፡፡
አየር መንገዱ የማክሮ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት በመሆን ማገልገል የሚችል ሲሆን፤ በተለይም ንግድ እና ቱሪዝምን በማሳለጥ ረገድ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ጠቁማለች፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ከጋዜጠኛዋ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመት 22 ሚሊየን ዓለም አቀፍ ደንበኞች በረራ ያደርጋሉ ብለዋል፡፡
የተጓዥ ደንበኞች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ መበራከት የአየር መንገዱን የማስተናገድ አቅም በመፈታተኑ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ለማስጀመር መገዳዳቸውንም ጠቁመዋል፡፡
የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን በኢትዮጵያ ብሎም በአህጉሪቱ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድገው ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቻይና እና የእሲያ መደራሻዎች ከሌሎች ዓለማት አንጻር በቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፤ ሆኖም የአየር መንገዱን ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በቢሾፍቱ አቡሴራ የሚገነባው ግዙፉና ዘመናዊው አውሮፕላን ማረፊያ የካርጎ ተርሚናል የዓለም የንግድ ዕቃዎች እና የህክምና አቅርቦቶች ከአምራች ሀገራት ተነስተው ወደ ተጠቃሚዎች የሚሰራጩበት ዋነኛ የአየር ሎጂስቲክስ ማዕከል እንዲሆን ያደርገዋል።
እንደ አበባ፣ ፍራፍሬ እና ስጋ ያሉ የኢትዮጵያና የጎረቤት ሀገራት ምርቶች ሳይበላሹ በጥራትና በከፍተኛ ፍጥነት ወደ መላው ዓለም ገበያ እንዲደርሱ ያስችላል። ይህም ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የአየር ጭነት ማዕከልነቷን የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡
ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ኢንደስትሪ ውስጥ እንደ ዱባይ (DXB) እና ሲንጋፖር (Changi) ያሉ ታላላቅ የዓለም መገናኛ ማዕከላት ተርታ ያሰልፋታል።
ኢትዮጵያን የአፍሪካ ቁልፍ የአቪዬሽን መናኸሪያ በማድረግ ከአህጉራዊ የትራንዚት ማዕከልነት ወደ መላው ዓለም ስልታዊ መገናኛ ድልድይነት ያሸጋግራል፡፡
04/08/2026
ሰበር ዜና :- በቪኒሲየስ ጁኒየር እና በሪያል ማድሪድ መካከል ወሳኝ ስብሰባ ሊካሄድ ነው!
በቪኒሲየስ ጁኒየር እና በሪያል ማድሪድ መካከል ያለው የወደፊት የኮንትራት ሁኔታን የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጥበት ሳምንት ደርሷል!
ታዋቂው የስፖርት ጋዜጣ The Athletic (ማሪዮ ኮርተጋና) እንደዘገበው፡ በዚህ ሳምንት በሪያል ማድሪድ የበላይ አካላት እና በቪኒሲየስ ወኪሎች መካከል በጣም ወሳኝ የሆነ የፊት ለፊት ውይይት ይደረጋል።
1. የብራዚላዊው ኮከብ አሁን ያለው ውል እ.ኤ.አ. ሰኔ 2027 ያበቃል። ማድሪዶች ተጫዋቹ ወደ መጨረሻው የውል ዓመት ከመግበቱ በፊት አዲስ ውል ማራዘም ይፈልጋሉ።
2. ቪኒሲየስ ቀደም ሲል በዓመት እስከ 30 ሚሊዮን ዩሮ የሚደርስ ክፍያ (የቀጥታ ደሞዝ፣ የጥቅማጥቅም እና የውል ማደሻ ቦነስ) ይጠይቅ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን ስምምነት ላይ ለመድረስ ሲል ጥያቄውን ለመቀነስ ፍቃደኛ ሆኗል።
3. ክለቡ በውል ማደሻው ላይ ከስምምነት መድረስ ካልተቻለ ተጫዋቹ በነፃ ዝውውር እንዳያመልጣቸው በዚሁ የዝውውር መስኮት የመሸጥ አማራጭን ሊመለከቱ እንደሚችሉ ተዘግቧል።
እንደ አርሴናል ያሉ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የድርድሩን ሁኔታ በጥብቅ እየተከታተሉ ይገኛሉ።
ማድሪዲስታስ! ቪኒሲየስ አዲስ ውል ፈርሞ በሳንቲያጎ በርናቤው ይቀጥላል ወይስ ይሸጣል? አርሰናል የተመኘው ይስምርለት ይሆን ? አስተያየታችሁን ኮሜንት ላይ አስቀምጡ!
⚽️⚽️⚽️
Saro Tube
🏐🏐🏐
24/07/2026
ለቁልቢ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል ሐዋርያዊ ጉዞ ያደረጉት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በድሬዳዋ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።
ሐዋርያዊ ጉዞውን በማድረግ ላይ የሚገኙት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፣ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ሲሆኑ፤ ሌሎች ብፁዓን አባቶች ሊቃነ ጳጳሳትና የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ የሥራ ኃላፊዎችም የልዑካኑ አባላት ናቸው።
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳቱና ልዑካኑ ከድሬዳዋ ከተማ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ሲደርሱ፣ በክቡር የድሬዳዋ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ሐርቢ ቡሕ፣ ኮሚሽነር አለሙ መግራ እና በከተማዋ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አማካኝነት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የድሬዳዋ ፓሊስ ደማቅ በሆነ ወታደራዊ ስነ ስረአት እንዲሁም ባማረ ሁኔታ በፓሊስ ፈረሰኞች አቀባበል ተደርጓል።
19/07/2026
በሶማሌ ክልል ቀብሪበያህ ወረዳ ዛሬ ነጋት በደረሰው አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ 12 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ፣ 3 ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በዚህ አሳዛኝ አደጋ ህይወታቸውን ያጡትን ወገኖች ለመቅበር እየተደረገ ባለው የቀብር ሥነ ሥርዓት ደግሞ ሌላ አሳዛኝ ክስተት ተከስቷል።
መቃብሩ ሟቾችን በመቅበር ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ በመደርመሱ በውስጡ የተቀበሩ ሰዎችን ህይወት ለማትረፍ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሐመድ በአደጋው ስፍራ በመገኘ ትሁኔታውን በቅርብ እየተከታተሉ ነው።
07/07/2026
አርጀንቲና ግብፅን በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቀለች
በ16ቱ ሀገራት ጥሎ ማለፍ አርጀንቲና ከግብፅ ያደረጉት ጨዋታ፤ በአርጀንቲና 3 ለ 2 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
07/07/2026
ቁንጅና ሲለካ!
#ኢትዮጵያ
ፍጹም ውበት ከከምበታ ዞን ሀዳሮ ምድር!
ስሟ ኤልሳቤጥ ደስታ፤ ውበቷ ደግሞ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ። ድንገት ተገናኝተን አይን መሳብ ሳይሆን ልብን የሚማርክ ፍጹም ተፈጥሮን የታደለች።
ኢትዮጵያዊነት ውበት ነው!
📷Misiker Kebede
06/07/2026
የ‘ገበታ ለትውልድ’ መርሃ-ግብር ያፈራው ታላቅ ስኬት የአርባምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት
👉 ዘመናዊ ሪዞርቱ ከ1 ሺህ 300 በላይ ሰዎችን የሚያስተናግድ የስብሰባ አዳራሽና በሐይቅ ላይ የተገነባ ልዩ ተንሳፋፊ ሬስቶራንትን አካትቷል።
👉 የኮንፈረንስ ቱሪዝምን በማስፋፋት ኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ መድረኮች ማዕከል የማድረግ ርዕይን ያጠናክራል።
👉 ለአካባቢው ማኅበረሰብ ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጥሯል።
Category
Website
Address
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when Saro Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.
