Gonder first

Gonder first

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gonder first, Health/Beauty, gonder, Bahir Dar.

03/09/2022
Photos from Gonder first's post 03/09/2022
03/09/2022

ጎንደር ፣ደብረብርሃን ፣ ደባርቅ እና ሰመራ ዩኒቨርሲቲዎች በመደበኛው እና በተከታታይ የትምህርት መርሐ ግብር ተማሪዎች አስመረቁ።
-------------------------------------------------
ጎንደር ዩኒቨርስቲ በዛሬው እለት በመደበኛ እና በተከታታይ ትምህርት መርሐ ግብር በመጀመሪያ ድግሪ፣ በሁለተኛ ድግሪ እና በፒ.ኤች.ዲ ድግሪ መርሃ ግብሮቾ 3,927 ወንድ 1,600 ሴት በድምሩ 5,527 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን በአጠቃላይ በ2014ዓ.ም በሁለት ዘር 11 ሽህ 493 ተማሪዎችን አስመርቋል።

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት አስራት አፀደወይን (ፒ.ኤች.ዲ) በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት የዛሬ ተመራቂዎች ቀደም ካሉ አመታት ተመራቂዎች ልዩ የሚያደርጋቸው አካባቢ፣ ሃገራዊ እና አለም አቀፋዊ የሆኑ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮዊ ጫናዎችን ተቋቁመው ለዚህ በመቃታቸው ነው ብለዋል።

ተመራቂ ተማሪዎች ባገኛችሁት እውቀትና ክህሎት ተጠቅማችሁ ለዚህ ላበቃችሁ ህዝብ ትርጉም ያለው አስተዋፆ ለማበርከት የተግባር ሰው መሆን ይጠበቅባቸዋል ያሉት ዶ/ር አስራት ዛሬ የገባችሁትን ቃል ኪዳን አክብራችሁ የሃገር እድገት፣ ሁለንተናዊ ስላም ፣ሉአላዊነት እና ህልውና እንዲረጋገጥ ከምንም በላይ ሃገራችን በእናንተ ዘመን አንድነቷ ተጠብቆ ወደ ከፍታ ማማ እንድትወጣ ታሪካዊ አሻራችሁን እንድታስቀምጡ ሲሉ አደራ ብለዋል።

በመጨረሻም አንድነትና የህብረት ታሪካችንን አጥብቀን ይዘን ዘመኑ የሚጠይቀው አዳዲስ እሴቶች እየጨመረ የተረከብናትን አገር ብቻ ሳይሆን የተሻለች ኢትዮጵያ ለልጆቻቸው በማስረከብ የአባቶቻችን አደራ መወጣት አለብን። ከሁሉም በፊት የኢትዮጵያ ህልውና መረጋገጥ አለበት። ሁሉም በየተሰማሩበት መስክ በአገኘው አጋጣሚ የሃገሩ ዘብና ሰራዊት ሆኖ መቆም ይገባዋል ሲሉ ፕሬዝዳንቱ መልክታቸው አስተላልፈዋል።

በተመሳሳይ ደብረብርሃን ፣ደባርቅ እና ሰመራ ዩኒቨርስቲዎችም በዛሬው ዕለት አስመርቀዋል።

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 928 ተማሪዎች አስመርቋል።

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 326 እንዲሁም ሰመራ ዩኒቨርስቲ ከ1000 በላይ ተማሪዎች አስመርቀዋል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በተከታታይ፣ በክረምት እና በማታ መርሃ ግብሮች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

03/09/2022

ተጠናቀቀ !!!!!

🇷🇼 ሩዋንዳ 0-1 ኢትዮጵያ 🇪🇹

(22' ዳዋ ሆቴሳ)

ኢትዮጵያ በአልጄርያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ውድድር ማለፋን አረጋገጠች።

በመጨረሻው ዙር ማጣርያ ሩዋንዳን የገጠመው ብሔራዊ ቡድናችን ከሜዳው ውጪ ባሳካው ድል በድምር ውጤት 1-0 አሸንፎ የቻን ማጣርያ ጉዞውን ምንም ሽንፈት እና ጎል ሳያስተናግድ በድል አጠናቋል።

እንኳን ደስ አለን !

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

03/09/2022

የዋልያዎቹ አሰላለፍ ይፋ ሆኗል

10 ሰዓት ላይ ከሩዋንዳ አቻው ጋር ወሳኝ የቻን የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቀዳሚ አሰላለፍ ታውቋል።

ብሔራዊ ቡድኑ ከመጀመሪያው የሩዋንዳ ጨዋታ ቸርነት ጉግሳን የመጀመሪያ የነጥብ ጨዋታውን በቋሚነት በዋናው ቡድን በሚያደርገው ይገዙ ቦጋለ ለውጦ ወደ ሜዳ ይገባል።

ግብ ጠባቂ

ፋሲል ገብረሚካኤል

ተከላካዮች

አስራት ቱንጆ
ምኞት ደበበ
ሚሊዮን ሰለሞን
ረመዳን የሱፍ

አማካዮች

ጋቶች ፓኖም
አማኑኤል ዮሐንስ
ከነዓን ማርክነህ

አጥቂዎች

አማኑኤል ገብረሚካኤል
ዳዋ ሁቴሳ
ይገዙ ቦጋለ

03/09/2022

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ...አሁን

የህክምናና ጤና ሳይንስ የዶክትሬት ተመራቂዎች
ነሐሴ 28/2014 ዓ.ም

03/09/2022

ፍትህ ከመቃብር በታች የመሆኗ ዋነኛ ማሳያ

03/09/2022

!

የሸዋሮቢት ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው አሁን ከመሸ 3:00 ሰዓት አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ሀይሎች ጥቃት ተፈፅሞበት ህይወቱ እንዳለፈ ታውቋል።

ነፍስ ይማር!

03/09/2022

በምክኒያት የተፈጠረ የሰው ልጅ ያለምክኒት አይወለደም፤ በማወቅም ይሁን በስህተት ወደ ዚህች ምድር የሚመጣ ሰው ሁሉ የአለምን አንድ ክፍተት ይደፍን ዘንድ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የታሰበ ነው፤
በኤርሚያስ 1፥5 ላይ "ከሆድ ሳልሰራህ አውቄሀለው" እንደሚል በእናቴ ሆድ ሳይሰራኝ እና ከ ማህጸኗ ሳልወጣ የሚያውቀኝ ሀያሉ አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ዛሬም ለልደት ቀኔ አድርሶኛል፤
ነሐሴ 27 የተወለድኩበት ቀን ነው! በእስካሁን ዘመኔ በምህረቱ ደግፎ በቸርነቱ ያቆመኝ የድንግል ማርያም ልጅ የተመሰገነ ይሁን። አሜን!!!❤
የልደት ቀን መልእክቴ፦
የሚል ነው።
ዳኜ ዋለ ያባቱ ልጅ (ጥቁሬ )
ነሀሴ 27 '2014
አዲስ አበባ_ኢትዮጲያ

01/09/2022

ቦሌ አራብሳ ኮንዶሚንየም በሰራተኛው የተገደሉ ሁለቱ ህፃናት!
ነፍስ ይማር
ለወላጆች መፅናናትን ይስጥልን

01/09/2022

በአዲስ አበባ ከተማ አንዲት የቤት ሠራተኛ ሁለት ህጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደለች በኋላ በቁጥጥር ሥር መዋሏን ፖሊስ አስታወቀ።

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Bahir Dar?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Gonder
Bahir Dar