Tis issat Fasil bridge

Tis issat Fasil bridge

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Tis issat Fasil bridge, Health/Beauty, Amhara, Bahir Dar.

በአፄ ፋሲል በ17ኛው መቶ/ክ/ዘ በአባይ ወንዝ ላይ የተገነባው የመጀመሪያው ድልድይ ከፈተኛ ጉዳት የደረሰበት መሆኑ በባለሞያ ጥናት የተረጋገጠ ስለሆነ ድልድዩ ቅርስነቱን ጠብቆ እንዲቀጥል ለመጠገን ለሚደረገው የሀብት ማሰባሰቢያ እንዲውል የተከፈተ ገፅ ነው ።

Photos from Tis issat Fasil bridge's post 23/01/2026

"ጥርን በባሕርዳር" የባህል አልባሳት ፋሽን ሾው ተካሄደ፤

የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ባህል ፣ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ አቶ ጋሻው እንዳለው በባህል አልባሳትና ጌጣጌጥ ፋሽን ሾው ዝግጅት መክፈቻ እንደተናገሩት የመላ ሀገራችን እውቅ መገለጫዎች ሆነው ግን ትኩረት ያነሳቸው ባህላዊ ሀብቶችን እየለዩ እና ከዘመናዊው ጋር በማስተሳሰር እንደገና እንዲንሰራሩ የማድረግ ተግባር እየተከናወነ ነው ብለዋል።

በተለይም "ጥርን በባሕርዳር" በሚል ልዩ ዝግጅት የውቧ ባሕርዳር ቀደምት መገለጫዋ የሆኑ እምቅ ሀብቶች በማውጣት በኩል ልዩ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ እንደሆነ ገልፀዋል።

ውቧ ከተማ ባሕርዳር ያሏትን ባህላዊና ቁሳዊ እሴቶችን ከከተማዋ እድገት ጋር አያይዞ በማሳደግ የባህል አልባሳትና ጌጣጌጥ ፋሽን መገኛ ማዕከል ማድረግ የሁላችን ትኩረት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

Photos from Tis issat Fasil bridge's post 22/01/2026

ጥርን በባህርዳር "የታንኳ ቀዘፋ ውድድር "
14/05/2018

Photos from Tis issat Fasil bridge's post 15/01/2026

በባህርዳር ከተማ አስተዳደር በጢስ አባይ መሪ ማዘጋጃ ቤት ስር የሚገኘውን የጥንታዊ ቅርስ የአፄ ፋሲል ድልድይ ጥገና ሀብት ማሰባሰብ ተጀምሯል ።
የአካውንት ቁጥር
ንግድ ባንክ -1000738432448
አማራ ባንክ -9900047695361
የአፄ ፋሲል ድልድይ ጥገና ብለን ማስገባት እንችላለን

Photos from Tis issat Fasil bridge's post 14/01/2026

🌐ጥርን በባህርዳር የጀልባ ሽርሽር በጣና ሐይቅ ተካሄደ።
ጥር 6ቀን 2018 ዓ.ም

በጣናነሽ ቁጥር 2 እና ንጋት ጀልባወች የተካሄደው የጀልባ ሽርሽር የሃይማኖት አባቶች፣ የልዪልዪ ተቋማት ተወካዮች ፣የቱሪስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ሀላፊወች; ልዪ ልዪ የቱሪዝምና የኪነጥበብ አደረጃጀት ተወካዮች ; መምህራን እና የአገርህን እወቅ ክበብ ተማሪወች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በሽርሽሩ ጣና ሐይቅና ልዩልዩ ጀልባወች እንዲሁም ዘመናዊ ሆቴል ሪዞርት ስራወች የተጎበኙ ሲሆን ለቀጣይ የውሐ ትራንስፖርት እና የቱሪዝም ስፍራወች ለሚጎበኙ አካላት ትውውቅ የፈጠረ ነው።

Photos from Tis issat Fasil bridge's post 11/01/2026

ጥርን በባህርዳርና ብስክሌት

Photos from Tis issat Fasil bridge's post 03/01/2026

የጥርን በባህርዳር መርሃግብር አንዱ አካል የሆነው የባህልና የኪነ ጥበብ ፌስቲባል በደመቀ ሁኔታ በባህርዳር ከተማ መከበር ተጀመረ
ሁሌም በየአመቱ የሚከበረው ጥርን በባህርዳር መርሐ ግብር አንዱ አካል የሆነው የባህልና ኪነ ጥበብ ፌስቲቫል ተከፈተ
ሁሉም ክፍለ ከተሞች የመስህብ ሀብታቸውን ይዘው በትይንታዊ ሰልፋ በጋራ ፌስቲባሉን ለመታደም በትይንታዊ ሰልፍ ወደ መርሃግብር ጉዞ ጀምረዋል ።

Photos from Tis issat Fasil bridge's post 31/12/2025

ቅርሱን ከጉዳት እንታደገው!

በ17ኛው መቶ ክ/ዘመን እንደተገነባ የሚታወቀውና በአባይ ወንዝ ላይ የመጀመሪያው ድልድይ የሆነው የአፄ ፋሲል ድልድይ ከጢስ ዓባይ ፏፏቴ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ለረጅም ዓመታት ለቱሪዝም ዘርፉ ዕድገት እያበረከተ ካለው አስተዋፅኦ በተጨማሪ የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በማሳለጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ይሁን እንጂ ይህ ጥንታዊና ታሪካዊ ድልድይ ለረጅም ዓመታት ምንም አይነት ጥገና ያልተደረገለት በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት ለከፍተኛ አደጋ የተጋለጠ ስለመሆኑ በዘርፉ ሞያተኛ በተደረገ የጉዳት መጠን ልየታ ጥናት ተረጋግጧል።
ጉዳቱንም በዘላቂነት ለመቅረፍ የባህርዳር ከተማ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ከአብክመ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመቀናጀት በጀት የተመደበ ቢሆንም የጥገና ስራው ከሚጠይቀው ወጭ አንፃር የህብረተሰባችንን ተሳትፎ በእጅጉ የሚጠይቅ በመሆኑ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ፣ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና ድርጅቶች ትብብር ታደርጉልን ዘንድ እየጠየቅን ይህንንም ሊያስተዳድር የሚችል ከባለሙያ እና ከተቆርቋሪዎች በተወጣጣ የተደራጀ ጥምር ኮሚቴ የባንክ አካውንት የተከፈተ ሲሆን ከዚህ በታች በተጠቀሱት የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች የምትችሉትን ያህል ድጋፍ ታደርጉልን ዘንድ በአከብሮት እንጠይቃለን።

የአፄ ፋሲል ድልድይ ቅርስ ጥገና ኮሚቴ

👉የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000738432448
👉 አማራ ባንክ 9900047695361

24/12/2025
Photos from Tis issat Fasil bridge's post 22/12/2025

የአፄ ፋሲል ድልድይ
አፄ ፋሲል መርቀው ድልድዮን ለአገልግሎት ይፋ ሲያደርጉ ጥበቃውን እንክብካቤውን በተመለከተ በጎንደርም መሻገሪያ በጎጃምም መሻገሪ ያላችሁ የአካባቢው መሳፍንቶች መኳንንቶች እና ባላባቶች ድልድዩን አደራ ሰጠው እንደሄዱ ታሪክ ያስረዳል ።
በመሆኑም በሰዐቶ የነበሩ መኳንንቶች ና ባላባቶች እራሳቸው ተደራጅተው መንግስት ትጥቅናተተኳሽ ልብስ ና መለዮ እያቀረበ ድልድዩ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት አንስቶ እስከ ኢህዴግ እስኪ ገባ ድረስ የአካባቢው ማህበረሰብ ቢያንስ ከአንድ ቤተሰብ አንድ አየተወከለ ጉዳት እንዳይደርስበት ሲጠበቅ ኑሯል። ይኸ ሂደት በቅብብሎሽ እሰከ አፄ ኃይለስላሴ ደረስ ደርሰ በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመን ቢሮ ተገንብቶ ፏፏቴውንም ድልድዮንም ለመጎብኘት የሚመጡ እንግዶች ተገቢ ጥበቃ ተደርጎላቸው የሀሳብ መስጫ መዝገብ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ የደረግ ነበር ። በዚሁ ዘመን የድልድዩ ኃላፊ የነበሩት ባሻ ፍቃድ ፏፏቴው ላይ ሆቴል ለመገንባት ፈንድ አግኝተው እንቅስቃሴ ጀመረው የነበረ ቢሆንም በውስጥ ችግር ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል እሰከ ደርግ ዘመን መንግስት ማብቂያ ቀጠለ
ነገር ግን
ደርግ- ኢህአዴግ ወደ መሀል አገር እየቀረበ ሲመጣ ጠላት እንዳይሻገር በማለት ድልድዮን ለመሰበር ወስነኖ ደማሚት ሲጠምድ በባሻ ፍቃድ አቸነፍ አስተባባሪነት ማህበረሰቡ የደርግን ጀነራሎችን ቀርበው ጠላትን በጋራ መዋጋት እንችላለን ድልድዮን ግን ማፍረስ አትችሉም ብለው መሳሪያ ሲማዘዙ
ደርግ ከማህበረሰቡ ጋር መጣላቱን ፈርቶ አሳቡን ቀይሮ ድልድዩም ሳይጎዳ ቀርቷል።
ለወትሮውም ከባላባቱና መኳንንቱ ቄም ያለበት ኢህዴግ ከ 1983 ጀምሮ አይደለም ትጥቅናተተኳሽ ልብስና መለዮ ሊያቀርብ እነዚህን ባላባቶች ፊውዳል ቢሮክራት እያለ እያሰረ ያሳድዳቸው በመጀመሩ ጥበቃው ና እንክብካቤ ተቋርጠ።
ይኸው ለከፍተኛ ጉዳት ተዳረገ።
በንጉሡ ና እስከ ደርግ ዘመነ መንግስት ማብቂያ አካባቢ ድረስ ድልድዩን የጠበቁ ከሞላ ጎደል እነዚህ ናቸው።
የአፄ ፋሲል ድልድይ የጠበቁ መኳንንቶች በየጎጡ
🧥ወፍ አርግፍ
1. ባሻ ፍቃዱ አቸነፍ ..ኃላፊ
2. ካሳ ጠገነው
3. ተገን ንብረት ኃላ ምትኩ ንብረት የተካ
4. አሰፋ ኪዳኑ ኃላ መኮንን ኪዳኑ የተካ
5. አብርሃም ገበያው
6. ጓዴ አፈወርቅ
7. ባሻ እምሩ በኃላ በጌታቸው እምሩ
8. ደጀን ኃይሌ
9. በላይ ቢተው

🧥ታምሬ ዘሞቻ
1.ገበይ ተፈራ
2. ተረዳ ከበደ
3.ወንዴ አለባቸው
4. ቢታረቅ ጀንበሬ
5. እንግዳው ወርቁ
6.አለም አላምሬ
7. በሌ ጎበዜ
8. መከተ እውነቱ
9.አምበል አደመ
10. እክመው አበሻ
11. ኪዳኑ መኮንን
ጢስ አበይ
1. ማንደፍሮ ይመር
2. ታደሰ አለሙ
3. አምባቸው ወርቁ
4. አምበየ ያዜ
ቡርቃ
1. ሙጨ ነጋሽ
2. ኃይሉ ብሬ
3. ንጉሴ አረጌ
4. ፈንታ ገደፈው
5.ፈጠነ ቢሻው በኃላ እውነቴ ቢሸው የተተካ
የግንድ ምሳኒትመንደል
1. ጋሻ አለሙ
2.ክንዱ መንገሻ
3.ይግዛው ዋሴ
4. ጎዳዴ አስፈው
5. ባይሌ መኮንን
ይኸ በእንዲህ እያለ የጣሊያን ወረራ እንዳለቀ ቀኝ አዝማች አለሙ አግደው በወቅቱ የአካባቢው አጥቢያዎች ዳኛ ኃይሉ መልሶ እስኪ ደራጅ በጎበዝ አለቃ አስጠብቀውት እንደነበር ይነገራል
እነሱም
1. አስር አለቃ አለባቸው ሻረው
2.ክብረት አቡነህ
3.ገበይ ተፈራ
4. ያረጋል አለሙ
5. ከፍያለው ሻረው
6. ይሁኔ ታምሩ
7. ዘሬ አለባቸው
8. ስመኘው መለሰ
ናቸው ይህን ታሪክ የተፃፈ ለመነሻነት እንጂ ሙሉ ላይሆን ይችላል ዋጋ እየከፈሉ የጠበቁ የተረሳ ካለ የምታውቁትን ጨምሩ
ምንጭ
ተራዳ ከበደ
መልኬ ንብረት

Photos from Tis issat Fasil bridge's post 20/12/2025

The Alata Bridge (or Yefasil Dilidy) is a historic 17th-century stone bridge near Blue Nile Falls (Tis Abay) in Ethiopia, famous for its traditional architecture, built under Emperor Susenyos with Portuguese/Indian craftsmen, and serves as a key landmark and photo spot on the walking path to the falls, showcasing Gondarian heritage.
Key Details:
Location: Near Tis Abay, close to Bahir Dar, Ethiopia, crossing the Alata River, a tributary of the Blue Nile.
History: Constructed in 1626 by Indian craftsmen for Emperor Susenyos (reigned 1607-1632).
Significance: One of Ethiopia's oldest stone bridges, representing Gondarian architectural heritage.
Tourism: A popular stop for visitors on the footpath to viewpoints of the Blue Nile Falls, offering stunning perspectives.
Features: An eight-arched stone structure, about 64m long and 2m wide, with the widest arch spanning 8m.
In essence, the Alata Bridge is a historical marvel and cultural treasure, connecting visitors to the powerful Blue Nile landscape and Ethiopia's rich past.
Lake Tana Island Monasteries and its Adjacent Wetland ...
The Alata Bridge known as Yefasil Dilidy (Bridge of Fasilades), is one of the cultural heritages located around Lake Tana. This br...

UNESCO World Heritage Centre
The Blue Nile Falls & Gorge - Visit Ethiopia
From the village of Tis Abay, a splendid series of full-frontal viewpoints can be reached along a 1.5km footpath across the 17th c...

Visit Ethiopia

Ethiopia, Amhara Region, Bahir Dar, Tissisat, Alata Bridge over Blue ...
Ethiopia, Amhara Region, Bahir Dar, Tissisat, Alata Bridge over Blue Nile River built by Portuguese for Emperor Susenyos in1626.

Alamy

Show all

18/12/2025

Lake Tana (Amharic: ጣና ሐይቅ, romanized: T’ana ḥāyik’i; previously transcribed Tsana[1]) is the largest lake in Ethiopia and a source of the Blue Nile. Located in Amhara Region in the north-western Ethiopian Highlands, the lake is approximately 84 kilometres (52 miles) long and 66 kilometres (41 miles) wide, with a maximum depth of 15 metres (49 feet),[2] and an elevation of 1,788 metres (5,866 feet).[3] Lake Tana is fed by the Gilgel Abay, Reb and Gumara rivers. Its surface area ranges from 3,000 to 3,500 square kilometres (1,200 to 1,400 square miles), depending on season and rainfall. The lake level has been regulated since the construction of the control weir where the lake discharges into the Blue Nile. This controls the flow to the Blue Nile Falls (Tis Abbai) and hydro-power station.

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Bahir Dar?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address

Amhara
Bahir Dar
ATSEFASILBRIDGE