Menkorer Sub-city Communication
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Menkorer Sub-city Communication, Health/Beauty, Ehiopia, Debra Markos.
30/09/2026
በደ/ማርቆስ በመንቆ/ክ/ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ የሠላም፣የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ውይይት ተካሄደ።
ወቅታዊ ጉዳዩን አስመልክቶ የውይይት መድረኩን የመሩት የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ በለጠ፣የደ/ማርቆስ ስራና ክህሎት መምሪያ ም/ል ሃላፊ አቶ ዘሪሁን ደገፉ ፣የመንቆ/ክ/ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ገብሬ ልርሳቸው ሲሆኑ በወቅታዊ የሰላም፣የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል።
በውይይት መድረኩ ነጋዴው ማህበረሰብ ከወቅታዊ በሠላም፣ልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ያሉ ጥያቄዎችንና ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ያሏቸውን ሠላማችንን ለማስጠበቅ እንደ አማራ አንድ መሆን ያስፈልጋል፣ችግሮችን በጋራ መታገል ይገባል፣አገልግሎት አሰጣጦችን ማስተካከል አለብን፣የልማት ጥያቄዎች መመለስ አለባቸው፣ ለሥራ ፈላጊዎች የሥራ ዕድል መፍጠር ተገቢ ነው ፣ፋብሪካዎች መስፋፋት አለባቸው፣የኮሪደር ልማት፣ደብረ ማርቆስ እንደ ሌሎች አካባቢ ከተሞች ሊመጥናት በሚችል ደረጃ እንድትለማ መስራት ያስፈልጋል የሚሉና ሌሎች ሃሳቦች ተነስተዋል።
ለተነሳሱ ሃሳቦች ማብራሪያ የሠጡት የክ/ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ በለጠ እንደ ክ/ከተማ የተጀማመሩ የልማት ሥራዎች እንዳሉ ጠቅሰው የተነሳሱ ችግሮችን ግን ተቀራርበን ተገናኝተን ተወያይተን ካልፈታናቸው ሌላ አካል ሊፈታልን አይችል።ስለሆነም የሚቀድመውን የሠላም ችግር አስቀድመን በመፍታት የቀረውን በሂደት እንፈታዋለን ብለዋል።
ሌላው ማብራሪያ የሠጡት የደ/ማርቆስ ከተማ ሥራና ክህሎት መምሪያ ም/ል ሃላፊ አቶ ዘሪሁን ደገፉ ወደ አለፉት ችግሮች እንዳንመለስ መንግስትና የንግዱ ማህበረሰብ ተቀራርቦ በጋራ መስራት አበት ሲሉ ተናግረዋል።ያ ካልሆነ የነሳናቸው የልማት እና ሌሎች ጥያቄዎን ለመመለስ ያስቸግራልም ሲሉ አቶ ዘሪሁን አስረድተዋል።
መስከረም 20/2019ዓ.ም
መንቆረር ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን
የፌስ ቡክ ገጻችንን ለመወዳጀት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61577372172164&mibextid=ZbWKwL
29/09/2026
"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"
በደ/ማርቆስ በመንቆ/ክ/ከተማ በሃገር አቀፍ ደረጃ "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሃሳብ ልዩ ልዩ ተግባራት ሲከናወኑ የቆዩበት የ2018ዓ.ም በጀት ዓመት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የማጠቃለያ አፈጻጸም ግምገማና የ2019ዓ.ም የበጋ በጎ ፈቃድ ተግባራት ዕቅድ ትውውቅ መርሃ ግብር ተካሄደ።
የማጠቃለያ እና የዕቅድ ትውውቅ መርሃ ግብሩ የተካሄደው የደ/ማርቆስ ኢንቨስትመንት መምሪያ ሃላፊ አቶ ተመስገን ተድላ፣የመንቆ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ በለጠ፣የክ/ከተማው ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ማስረሻ ጸጋዬ ሌሎች የክ/ከተማና የቀበሌ አመራሮች እንዲሁም በጎ ፈቃደኞች በተገኙበት ነው።
በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ በክረምቱ የተከናወኑ የበጎ ፈቃድ ተግባሪራት አፈጻጸምና የቀጣይ 2019ዓ.ም የበጋ በጎ ፈቃድ ተግባራት ዕቅድ ትውውቅ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
ከውይይቱ በኋላ በክረምቱ የበጎ ፈቃድ ተግባር ላይ የተሳተፉ በጎ አድራጊ ተቋማት፣ግለሰቦችና አመራሮች የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
መስከረም 19/2019ዓ.ም
መንቆረር ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን
የፌስ ቡክ ገጻችንን ለመወዳጀት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61577372172164&mibextid=ZbWKwL
29/09/2026
በደ/ማርቆስ ከተማ በመንቆ/ክ/ከተማ ለቀበሌ 05 ምክር ቤት አባላት አሰራርን መሠረት ያደረጉ ስልጠናዊ ውይይት ተደረገ።
ስልጠናው የተሠጠው ከደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳደር አፈ ጉባ ጽ/ቤት ሲሆን የምክር ቤት አባላት ለብዙ ጊዜያት የነበሩ መደበኛ ስራወች ተቋርጠው ከመቆየታቸው አንጻር በምክር ቤት የነበሩ የቀበሌ አሰራሮችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ስልጠና ማስፈለጉ ተጠቅሷል።ስልጠናው የምክር ቤት አባላትን ለማጠናከር የተደረገ ነውም ተብላሏ።
የምክር ቤት አባላት ከስልጠናው ጋር በተያያዘ ባደረጉት ውይይት አሉ ያላቸውን የአሰራር፣ፍትሃዊ የሃብት ወይም የመልማት ጥያቄ፣አፈ ጉባኤዎች ቋሚ ኮሚቴ ኑሯቸው የልማት ስራዎችን እየገመገሙ መሄድ እንዳለባቸው፣የቀበሌውን የማዕድን ሃብት አጠቃቀም፣ ቀበሌው ፈጥኖ ወደ ተሻለ ልማት መግባት እንዳለበት፣መንግስት የህዝብን ወይም የምክር ቤቱን ድምጽ ማክበር ተገቢ እንደሆነ፣የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ቢዘጋጁ፣እንደ እኛ ክ/ከተማ የኮሪደር ልማት እየተሠራ አይደለም፣በገበያ ጥበት ምክንያት ሰው ለአደጋም እየተጋለጠ በመሆኑ መፍትሄ ቢፈለግለት ሲሉ መፍትሄ አዘል ጥያቄዎችን አንስተዋል።
የምክር ቤቱ አባላት በወርሃዊ የስብሰባ ቀን እየተገኙ ስለ ቀበሌው መምከር ተገቢ አንደሆነ የገለጹት የቀበሌ 05 አስተዳደር አቶ እንየው ፈንቴ ልማትን በተመለከተ የተነሱ ጥያቄዎች ትክክል መሆናቸውን ጠቅሰው ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ ግን የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
ከልማት፣ ከመልካም አስተዳደር እና ሌሎች የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ የምክር ቤት አባላት ሞጋችና አሳማኝ መሆን አለባቸው ሲሉም አስተዳዳሪው ተናገረዋል።
አቶ እንየው ፈንቴ ከመንቆረር ኮንስትራክሽን ድረጅት ጋር በተያያዘ ለተነሳው ጥያቄ ድረጅቱ እንደ ክ/ከተማና እንደ ከተማ አስተዳደር እየሠራ ያለው ስራ በጣም ጥሩ የሚባል መሆኑን ጠቅሰው መንቆ/ኮንስትራክሽን ድንጋይ ለማውጣት የቆፈረው ቦታ ለወደፊት ስጋት እንደሆነባቸው የምክር ቤት አባላት ያነሱት ሃሳብ ትክክል ነው የሚስተካከልበት መንገድ ይፈጠራል ሲሉ ተናግረዋል።
ለምክር ቤት አባላት የሚሰጡ ሥልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም የምክር ቤት አባላት በወቅታዊ የሠላምና የጸጥታ ሁኔታን በተመለከተ ውይይት አካሂደዋል።
መስከረም 19/2019ዓ.ም
መንቆረር ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን
የፌስ ቡክ ገጻችንን ለመወዳጀት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61577372172164&mibextid=ZbWKwL
26/09/2026
25/09/2026
በደ/ማርቆስ የመንቆ/ክ/ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት የ2018ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019ዓ.ም ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ።
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የክ/ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጸሐይ በለጠ ባለፈው ዓመት 2018ዓ.ም በነበረው አፈጻጸም በርካታ ህገ ወጥ ነጋዴዎች ወደ ህጋዊ መስመር እንዲገቡና ብዙ ሥራዎች የተፈጸሙበት እንደሆነ ገልጸው በዚህ ዓመት የታቀደው ዕቅድ ላይም በመግባባት እቅድን ቆጥሮ በመስጠትና ቆጥሮ በመቀበል ለተፈጻሚነቱ መትትጋት እንደሚገባ አመላክተዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚው መድረኩን በንግግር ከከፈቱ በኋላ የ2018ዓ.ም አጻጸምና የ2019ዓ.ም ዕቅድ በጽ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ገብሬ ልርሳቸው ቀርቦ ከባለሙያዎችና ከአጋር አካላት ጋር ውይይት ተደርጎበታል።በእቅዱ ላይ የጋራ መግግባባት በመፍጠር እንፈጽመዋለን በሚል መንፈስ የፊርማ ስነስርዓት ተካሂዷል።
በመድረኩ ዋና ስራ አስፈጻሚውን ጨምሮ አጋር አካላትና የመምሪያ ንግድና ገበያል ልማት ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
መስከረም 15/2019ዓ.ም
መንቆረር ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን
የፌስ ቡክ ገጻችንን ለመወዳጀት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61577372172164&mibextid=ZbWKwL
24/09/2026
በደ/ማርቆስ የመንቆ/ክ/ከተማ ማህበራዊ ዘርፍ ጽ/ቤት "እንክብካቤና ዘላቂ ደህንነት ለአረጋውያን መልካም ህይወት" በሚል መሪ ቃል የአረጋውያንን በዓል አከበረ።
የ2019ዓ.ም የአረጋውያን በዓል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ36ኛ በሃገራችን ደግሞ ለ35ኛ ጊዜ ነው በክ/ከተማው የተከበረው።የበዓሉ መከበር ዋና ዓላማ አረጋውያን ለሃገርና ህዝብ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ በመዘከር፣እውቅና በመስጠትና በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴና ተሳትፏቸው ላይ ተጽዕኖ የሚያደርሱ ጉዳዮችን በመፈተሽ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እንዲቻል የተደረገ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በውሳኔ ሰጭነት ላይ ሰፊ ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሆነ በቀረበው አጭር ሰነድ ላይ ተመላክቷል።
ሰነዱ ከቀረበ በኋላ አረጋውያን በክ/ከተማው በኩል ስለሚመጡ ድጋፎች፣ስለማህበሩ መመስረት ጥቅምና ሌሎችን ሃሳቦች አንስተዋል።
ለተነሱ ሃሳቦች ማብራሪያ የሠጡት የክ/ከተማው ማህበራዊ ዘርፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዘመኑ ተመስገን አረጋውያን ለዚህ ትውልድ የእውቀት፣የፍቅር፣የሥነ-ምግባር፣ የታሪክና የትውፊት እንዲሁም የእሴት ምንጭ በመሆናቸው በዚህ ዘመን ያለ ትውልዱ ከእነሱ የሚማረው ብዙ ነገር ነው።በመሆኑም አረጋውያንን መንከባከብ የሁላችንም ሃላፊነት ነው ብለዋል።
አቶ ዘመኑ የማህበሩ መመስረት የአረጋውያንን መብት ለማስጠበቅ የተደረገ ነው። ከዚህ አንጻር የማህበሩ ኮሚቴ ከክ/ከተማው እስከ ሃገር አቀፍ ድረስ አረጋውያንን በተመለከተ ያሉ እንቅስቃሴዎችን በንቃት እየተከታተለ ከሚመለከተው አካል ጋር መስራት አለበት ብለዋል።
በመድረኩ የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ በለጠ፣አቶ ዘመኑ ተመስገን እንዲሁም ከክፍለ ከተማው የተውጣጡ አረጋውያን ተገኝተዋል።
መስከረም 14/2019ዓ.ም
መንቆረር ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን
የፌስ ቡክ ገጻችንን ለመወዳጀት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61577372172164&mibextid=ZbWKwL
24/09/2026
በደ/ማርቆስ የመንቆረር ክ/ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት የማኔጅመንት ቡድን አባላት በጽ/ቤቱ የ2019ዓ.ም በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ።
ከውይይቱ በኋላ ለግቡ መሳካት የማኔጅመንት አባላቱ የጋራ የስምምነት ፊርማቸውን አስቀምጠዋል።
የፊርማ ዋና አላማ የታቀደውን ዕቅድ በጋራ እናሳካዋለን የሚል መሆኑንም የቡድኑ አባላት ገልጸዋል።ውይይቱ የተካሄደው የጽ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ጌታ ተገኘ በተገኙበት ነው።
መስከረም 14/2019ዓ.ም
መንቆረር ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን
የፌስ ቡክ ገጻችንን ለመወዳጀት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61577372172164&mibextid=ZbWKwL
21/09/2026
በደ/ማርቆስ የመንቆ/ክ/ከተማ አስተዳደር የ2018ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ አካሄደ።
ክ/ከተማው የእቅድ አፈጻጸም ግምገማና ትውውቁን ያደረገው አጠቃላይ ከቀበሌ እስከ ክ/ከተማ ያሉ አመራሮችና ባለሙያዎች በተገኙበት ነው።
በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ በለጠ በክፍለ ከተማው የተከናወኑ ዋና ዋና የልማት ስራዎች፣ የህዝብ ተጠቃሚነትን ያረጋገጡ መሰረተ ልማት ግንባታዎች እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈጻጸሞች ውጤታማ እንደነበሩና ብዙ አመርቂ ሥራዎች እንደተመዘገቡ ገልጸዋል።
አቶ ፀሐይ ለባለፈው ዓመት ውጤታማ ለመሆናችን የአመራሩ የማስተባበር ብቃት፣ የባለሙያው ብርታትና ትጋት እንዲሁም የማህበረሰቡ ድጋፍ ወሳኝ ነበር። ለዚህም ለሁሉም አካላት ምስጋና ይገባል ብለዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለው የ2019ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድን ሳይንጠባጠቡ በመፈጸም ከባለፈው ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ለማምጣት ትውውቁን በአግባቡ መከታተል እንደሚገባ በመክፈቻ ንግግራቸው ጠቁመዋል።
ከዚህ በመቀጠል የ2019ዓ.ም በክ/ከተማው አስ/ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታ ተገኘ አጠቃላይ የክ/ከተማው የየተቋማት ዕቅድ ዓላማ፣ግብና የመፈጸሚያ ስልቶችን በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ከውይይቱ በኋላ ባለፈው ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም የተሻለ በማምጣት በመምሪያ ደረጃ የተሻለ አፈጻጸም ላመጡ ተቋማትና በክ/ከተማው በኮሚቴነትና በሌሎች ስራዎች ልዩ አስተዋጽኦ ላደረጉ ባለሙያዎች የገንዘብ፣የጋቢ ሽልማትና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።
የክ/ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ በለጠ በክፍለ ከተማው እያደረጉ ላሉት አስተዋጽኦ የሙሉ ሱፍ ሽልማትና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸው ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
መስከረም 11/2019ዓ.ም
መንቆረር ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን
የፌስ ቡክ ገጻችንን ለመወዳጀት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61577372172164&mibextid=ZbWKwL
07/09/2026
ተማሪዎችን በወቅቱ እናስመዝግብ
ትምህርት ማለት ሰው እውቀት፣ ክህሎት፣ ግንዛቤና ልምድ የሚያገኝበት የመማርና የማስተማር ሂደት ነው።
በቀላሉ፦ ትምህርት ማለት ነገሮችን ማወቅ ብቻ ሳይሆን፣ ያወቅነውን በተግባር መጠቀምና ራሳችንን ማሻሻል ነው።
ለምሳሌ፦በት/ቤት ማንበብና መጻፍ መማር፣ሂሳብ መማር፣ ኮምፒውተር መጠቀም መማር፣ ሙያ መማር፣ከልምድና ከሕይወት መማር ነው።
ስለዚህ ትምህርት እውቀት + ክህሎት + ልምድ + ግንዛቤ ማለት ይቻላል።
ትምህርት በሰው ሕይወት በጣም ትልቅ ጥቅም አለው። ዋና ዋናዎቹ፦ እውቀትን ይጨምራል – ዓለምንና ነገሮችን በትክክል እንድንረዳ ያደርጋል።
የሥራ ዕድልን ያሳድጋል – ሙያና ክህሎት እንድንገነባ ይረዳል።
የገቢ አቅምን ያሻሽላል – በተሻለ ሙያ መሥራትና ገቢ ማግኘት ያስችላል።
ችግር መፍታትን ያስተምራል – ነገሮችን በማስተዋልና በማሰብ ውሳኔ እንድንሰጥ ያግዛል።
መግባባትን ያሻሽላል – ሀሳባችንን በግልጽ ለሌሎች እንድናስተላልፍ ይረዳል።
የግል እድገትን ያመጣል – በራስ መተማመንና ኃላፊነት ያዳብራል።
ለማኅበረሰብ ያገለግላል – የተማረ ሰው ለቤተሰቡ፣ ለሥራ ቦታውና ለሀገሩ የተሻለ አስተዋጽኦ ማድረግ ይችላል።ትምህርት ሰውን የተሻለ ማሰብ፣ መሥራት፣ መወሰን እና ሕይወቱን ማሻሻል እንዲችል ያደርገዋል።
ትምህርት ለሀገር እጅግ ትልቅ ጠቀሜታ አለው።
የሀገር ልማትን ያፋጥናል – የተማሩ ሰዎች በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በቴክኖሎጂና በሌሎች ዘርፎች ያበረክታሉ።
ብቁ የሰው ኃይል ያፈራል – ዶክተሮች፣ መምህራን፣ መሐንዲሶች፣ ሳይንቲስቶችና ሌሎች ባለሙያዎችን ያፈራል።
ኢኮኖሚውን ያጠናክራል – ምርታማነትንና የሥራ ዕድልን ያሳድጋል።
ፈጠራን ያበረታታል – አዳዲስ ሀሳቦችና ቴክኖሎጂዎች እንዲፈጠሩ ያግዛል።
መልካም ዜግነትን ያዳብራል – ሕግን፣ መብትንና ኃላፊነትን የሚያውቁ ዜጎችን ያፈራል።
ሰላምና መቻቻልን ያጠናክራል – ልዩነቶችን በመረዳት በሰላም መኖርን ያስተምራል።
ሀገርን በዓለም ያወዳድራል – በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና በኢኮኖሚ ተወዳዳሪ እንድትሆን ያግዛል።
ትምህርት ለሀገር የሰው ኃይል መሠረት ነው። የተማረ ዜጋ ራሱን ብቻ ሳይሆን ቤተሰቡን፣ ማኅበረሰቡንና ሀገሩን ያሳድጋል።
በመሆኑም ወቅቱ ተማሪ የሚመዘገብበት በመሆኑ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንዳይርቁ በአቅራቢያችሁ ባለ ትምህርት ቤት ለ2019ዓ.ም የትምህርት ዘመን እድሚያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ተማሪዎችን እንድታስመዘግቡ ስንል መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።
ጳጉሜን 2018ዓ.
መንቆረር ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን
የፌስ ቡክ ገጻችንን ለመወዳጀት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61577372172164&mibextid=ZbWKwL
Category
Website
Address
Debra Markos
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when Menkorer Sub-city Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.
