Geda Tokuam PHCU

Geda Tokuam PHCU

Share

GEDA TOKUMA Health Center Under Bishan guracha Sub City Oromia Region. Quality Health For All.

30/07/2026

አረንጓዴ ዐሻራ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የነበሩ መሪ ቃሎች....

🌳2011 ዓ.ም በአንድ ሰው 40 ችግኝ
🌳2012 ዓ.ም እየተጠነቀቅን እንተክላለን
🌳 2013 ዓ.ም ኢትዮጵያን እናልብሳት
🌳 2014 ዓ.ም ዐሻራችን ለትውልዳችን
🌳 2015 ዓ.ም ነገን ዛሬ እንትከል
🌳 2016 ዓ.ም የምትተክል ሀገር የሚፀና ትውልድ
🌳 2017 ዓ.ም በመትከል ማንሰራራት
🌳 2018 ዓ.ም ተስፋን እንትከል

Green ethiopia #ኢትዮጵያ

Photos from Geda Tokuam PHCU's post 30/07/2026

ብሔራዊ የRMNCAYH (የእናቶች፣ የጨቅላ ሕፃናት፣ የሕፃናት፣ የአፍላ ወጣቶችና እና ወጣቶች ጤና) ፖሊሲ ሰነዶች ማስተዋወቂያ መድረክ ተካሄደ
_________________________________
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ
በማስተዋወቂያ መድረኩ ላይ እንደተናገሩት፣ የእናቶችን እና የሕፃናትን ሞት ለመቀነስ የሚደረገው ጉዞ በጥሩ መንገድ ላይ ይገኛል ብለዋል። ይህም የተሳካው የመጀመሪያ ደረጃ ጤና እንክብካቤ አገልግሎትን በማጠናከር መሆኑን አስረድተዋል።

ለ2030 የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ከተደራሽነት ባሻገር ማሰብ እና ትኩረታችንን በአገልግሎት ጥራት እና በፈጠራ ላይ ማድረግ አለብን።

በመድረኩ ይፋ የተደረጉት 5 ሰነዶች ትግበራ አጋሮች ድጋፍ ማድረግ አለባቸው ያሉት ዶ/ር ደረጀ ዲጂታላይዜሽን እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የተሻሉ ውጤቶችን ለማስገኘት ትልቅ አቅም መፍጠራቸውን ተናግረዋል።

መድረኩ የተዘጋጀው በፖሊሲ እና በዲጂታል ፈጠራዎች አማካኝነት የዘላቂ ልማት ግቦችን (SDG) እና ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን (UHC) አጀንዳዎችን ለማስቀጠል ብሔራዊ የRMNCAH ፖሊሲ ሰነዶችን እና የዲጂታል መሳሪያዎችን ለማስተዋወቅ ነው።

ወደፊት የሚከናወኑ የRMNCAYH ተግባራትን ፈጠራ/Innovation/ በታከለበትና ትርጉም ባለው መልኩ ለመፈፀም እንዲያግዝ የጤና ሚኒስቴር፣ የክልል ጤና ቢሮዎች፣ ለጋሾችና አጋር ድርጅቶች፣ የሙያ ማህበራት እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ሰነዶቹ ተዋውቀዋል/Disseminated/።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም ሰነዶቹን ለመተግበር ቃል ገብተዋል።

source Ministry of Health,Ethiopia: moh.gov.et

24/07/2026
Photos from Geda Tokuam PHCU's post 24/07/2026

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አዳዲስ የጤና ተግዳሮቶችን በብቃት ለመወጣትና ይበልጥ ለማዘመን ጉዞውን በፈጠራ፣ በቴክኖሎጂ እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የታገዘ የዲጂታል ሽግግር ላይ የበለጠ ሊጠናከር ይገባል
_____________________________________
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት 100ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ከሐምሌ 9 እስከ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ ፕሮግራሞች በደማቅ ሁኔታ አከበረ።

በበዓሉ ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ፣ ኢንስቲትዩቱ በጤና ምርምር፣ በወረርሽኝ መከላከልና በሕዝብ ጤና ጥበቃ ረገድ የሀገር ኩራት በመሆን ያሳለፈውን የመቶ ዓመታት ስኬታማ ጉዞ አድንቀው፣ ተቋሙ በቀጣይም አዳዲስ የጤና ተግዳሮቶችን በብቃት ለመወጣትና ይበልጥ ለመዘመን ጉዞውን በፈጠራ፣ በቴክኖሎጂ እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የታገዘ የዲጂታል ሽግግር ላይ አሁን ከሚገኝበት በላይ ሊጠናከር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ዶ/ር ደረጄ መልዕክታቸውን ሲያጠቃልሉ “ታላቁ ስኬታችን ያለፈው ታሪካችን ብቻ ሳይሆን፣ በጋራ የምንገነባው የወደፊት እጣ ፈንታችንም ነው”በማለት የተቋሙ ቀጣይ ምዕራፍ በጠንካራ ትብብርና ጊዜውን በዋጁ ሳይንሳዊ ምርምሮች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የተካሄደው 5ኛው የሕብረተሰብ ጤና ሳይንሳዊ ኮንግረስ በርካታ ምርምሮችና ጥናቶች ቀርበውበት ሰፊ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፣ በማጠቃለያውም ለኮንግረሱና ለበዓሉ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለሙያዎችና አጋር አካላት የላቀ የእውቅና ሽልማት ተበርክቷል።

Website: moh.gov.et
source Ministry of Health,Ethiopia
july 2026gc

24/07/2026

TB

ሁለት ሳምንት እና ከዛ በላይ የቆየ ሳል፣ ክብደት መቀነስ እና ሲተኙ በላብ መዘፈቅ የቲቢ በሽታ ምልክት ሊሆን ስለሚችል በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራና ህክምና ያግኙ!


Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V

Photos from Ministry of Health,Ethiopia's post 24/07/2026

የአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል "በጎነት ለጤና፣ ፈውስ ለሁሉም" በሚል መሪ ቃል የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብሩን በይፋ አስጀምሯል
________

መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚና የሆስፒታሉ ቦርድ አባል አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ፣ መንግሥት በርካታ የበጎ ፈቃድ ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አስታውሰው ክፍለ ከተማው ከሆስፒታሉ ጋር በመቀናጀት ህብረተሰቡን ለማገልገል መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

የአእምሮ ጤና እክል ያለባቸውን ሰዎች ማከም ከፍተኛ የበጎነትና ተግባር ነው ያሉት አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ ሆስፒታሉ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብሩ ነጻ የጤና ምርመራ ማቅረቡ የሚያኮራ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

ክፍለ ከተማው ከጤና ሚኒስቴርና ከሌሎች ተቋማት ጋር በመቀናጀት የበለጠ የተጠናከረ ሥራ መስራቱን እንደሚቀጠልም አስታውቀዋል።

የአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር አቶ እዳኦ ፈጆ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለአገርና ለወገን ያለንን ሀላፊነት በተግባር የምናሳይበት የላቀ የዜግነት መገለጫ ነው ያሉ ሲሆን ሆስፒታሉ በዘንድሮው የክረምት የበጎ ፍቃድ መርሀ ግብር 67 ሺህ ሰዎችን ነጻ የጤና ምርመራና ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

በዚህም ባለሞያዎች በሙያዊ ስነምግባርና በባለቤትነት ስሜት ይህን አገራዊ ሀላፊነት እንዲሚወጡ ያላቸዉን እምነት ገልጸዋል።

Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V

Photos from Geda Tokuam PHCU's post 24/07/2026

እንኳን ደስ አላችሁ ! እንኳን ደስ አለን!

በ2018 በጀት ዓመት በጤናው ዘርፍ የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገብ እውቅና እና ሽልማት ያገኛችሁ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ እና የኦሮሚያ ጤና ቢሮ እንኳን ደስ አላችሁ ! እንኳን ደስ አለን ! ውጤቱ ሁላችንም የህዝባችንን የጤና ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ የሚያተጋን ፣ ወደ ላቀ ከፍታ ለመስፈንጠር የሚያነሳሳን በመሆኑ የጋራ ጥረታች የሚቀጥል ይሆናል! በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን! FMOH

23/07/2026

የሚዲያ አጠቃቀም ግንዛቤ በማሳደግ የተሳሳቱ የመረጃ ስርጭቶችን መከላከል፤ ለጋራ ሰላማችን መጠበቅ ሚናው ከፍተኛ ነው፡፡

🛜 መረጃን ከማጋራት በፊት የመረጃ ምንጮችን በማጣራት የተሳሳቱ መረጃዎችን መከላከል ተገቢ ነው፡፡

⚓️የሚዲያ ይዘትን በጥልቀት መረዳት፣
⚓️ ትክክለኛ መረጃን ከፕሮፓጋንዳ መለየት እና
⚓️ ሁከትን የሚቀሰቅሱ የውሸት ትርክቶችን በማጋለጥ ማህበራዊ ትስስራችን እና ዘላቂ ሰላማችን ልናሰፍን ይገባል፡፡

ሚዲያን
♟ ለልማት ሥራዎች
♟ ለሰላም ግንባታ እና
♟ ለማኅበራዊ ትስስር መሣሪያ አድርጎ መጠቀም ይገባል፡፡

⚠️ የሚዲያ ባለሙያዎች አንድነትን፣ መቻቻልን እና ገንቢ አመለካከቶችን የሚያበረታቱ ይዘቶችን በመፍጠር እና በማሰራጨት የጥላቻ ንግግር እና ከፋፋይ ትርክቶችን መከላከል ይኖርባቸዋል፡፡

✅ ወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ በመጠቀም በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ የጥላቻ እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ሪፖርት ማድረግ እና ብሔራዊ ጥቅሞቻችን የሚያጎሉ መረጃዎችን ተደራሽ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊

Photos from Geda Tokuam PHCU's post 23/07/2026

"መመርመር፣ መከታተል፣ መበልፀግ፣ ራስን መንከባከብ ጤናዎን በእጆዎ ያደርጋል!" በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የራስን ጤና በራስ የመጠበቅ ወር የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ
___

"መመርመር፣ መከታተል፣ መበልፀግ፣ ራስን መንከባከብ ጤናዎን በእጆዎ ያደርጋል!" በሚል መሪ መልዕክት የራስን ጤና በራስ የመጠበቅ ወር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ15ኛ በኢትዮጵያ ለ2ኛ ጊዜ ተከብሯል።

በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በስፋት በማህበረሰቡ ውስጥ እየተስተዋሉ የሚገኙ ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን አስቀድሞ ለመለየት፣ ለመከላከልና በወቅቱ ተገቢውን ህክምና ለመስጠት፣ የስነ ተዋልዶ፣ የእናቶች፣ የጨቅላ ህፃናትና ህፃናት እንዲሁም የአፍላ ወጣቶች ጤና እና ስነምግብ ላይ ያለውን የማህበረሰብ ግንዛቤ በማሳደግ ዜጎች የራሳቸውን ጤና በራሳቸው እንዲጠብቁ የንቅናቄ መድረኩ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው በጤና ሚኒስቴር የእናቶች ጤና ዴስክ አስተባባሪ የሆኑት ሲስተር ዘምዘም መሐመድ ገልፀዋል።

ዜጎች ቢያንስ በዓመት ሁለት ጊዜ የጤናቸውን ሁኔታ በመደበኛነት ለማወቅ በጤና ተቋም ተገኝተው አጠቃላይ የጤና ምርመራ ማድረጋቸው አስፈላጊ መሆኑን አክለው ተናግረዋል።

በፕሮግራሙ የፓናል ውይይት እና የአኖሌ እና ቦኩሸነን ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የመስክ ጉብኝት ተደርጓል።

Website: moh.gov.et
Ministry of Health,Ethiopia

23/07/2026

የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተጠባቂ ውጤቶች....

✍️ እንደሀገር ባልተግባባንባቸው እጅግ መሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት፤

✍️ቅቡልነት ያለውን ሀገረ-መንግስት ግንባታ ላይ ምክረ-ሃሳቦች ማቅረብ፤

✍️ የተጠናከረ ሀገራዊ አንድነት እና ማህበራዊ ትስስርን መፍጠር፤

✍️ የተሻለ የዲሞክራሲ እና የፖለቲካ ባህል መፍጠር፤

✍️ በሕዝብና በሕዝብ እንዲሁም በመንግስትና በሕዝብ መካከል የተሸረሸሩ እምነቶችን በመገንባት የተሻለ ግንኙነት መፍጠር፤


Ethiopian National Dialogue Commission/የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Shashemene?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Shashemene