Etcare
An official page of Etcare, Etcare is a company that produces and sell beauty care products
20/06/2026
ባህርዳር ዝግጁ?
እኛ ዝግጁ ነን
ነገ ለሚደረገው ታላቅ የደረጃ አሳኪውች የእውቅና መሰናዶ የኢቲኬር ባህርዳር ታላላቅ መሪዎች ዝግጁ ናቸው።
እናንተስ? ነገ በ አማራ ስቴት ዩኒቨርስቲ አዳራሽ እንገናኝ።
20/06/2026
ቀጥለናል
2ኛ ቀን የኢቲኬር ባህርዳር ቆይታ
የማለዳ ስልጠና በኢቲኬር ባህርዳር ቅርንጫፍ በድምቀት ተከናውኗል።
በኢቲኬር ማስተር አሰልጣኝ ኤሊት አምባሳደር ተመስገን ሀይሉ የተመራው ይህ ስልጠና የኢቲኬር ባህርዳር መሪዎችን ጨምሮ በርካቶች ተገኝተውበታል።
19/06/2026
ኢቲኬር ባህርዳር ቀን 1
ደማቁ የኢቲኬር ባህርዳር የስልጠና መሰናዶ ዛሬ አርብ ጅማሮውን አድርጓል።
በኢቲኬር ማስተር አሰልጣኝ እና ኤሊት አምባሳደር ተመስገን ሀይሉ መሪነት በኢቲኬር በባህርዳር ለሚገኙ ኢቲኬሪያንስ ድንቅ የስልጠና መሰናዶ እየተከናወነ ይገኛል።
17/06/2026
መሪነት በዚህ ድምቀት ተከናውኗል።
መሪነት የሚል ርእስን ይዞ በየሳምንቱ በተለያዩ ን ኡስ ርእሶች ቆይታ የሚያደርገው የስልጠና መድረክ ዛሬም በተልመደው ድምቀት በተለመደው የእውቀት እና የልምድ ከፍታ በድንቅ የመድረክ አያያዝ ታጅቦ በኢቲኬር ዋና መስሪያ ቤት አዳራሽ ተከናውኗል።
የኢቲኬር ማስተር አሰልጣኝ እና ኤሊት አምባሳደሩን ኢንጂነር ታጠቅ ጌታቸውን በመድረክ ይዞ የተገኘው ይህ የስልጠና መድረክ ለመሪነት የተጉ ሁሉ የተገኙበት ድንቅ ጊዜ ሆኖ አልፏል።
16/06/2026
በድምቀት በአብሮነት ልንሰባሰብ ቀን ተቆርጧል!
ደማቁ የኢቲኬሪያንስ የአብሮነት ቀን በ ጉለሌ የእፅዋት ማእከል
እሁድ ሰኔ 21
ከኢቲኬር ዋና መስሪያ ቤት ተነስተን በድምቀት እስከ መዳረሻችን ጉለሌ እፅዋት ማእከል በአብሮነት
በጉለሌ እፅዋት ማእከል የጋራ የቤተሰብ ጊዜ ከታላላቅ እንግዶች ጋር።
ሰኔ 21 እንገናኝ
16/06/2026
የመሪነት መድረካችን ተመልሷል።
ነገ በእለት ረቡእ ታላቁ አሰልጣኝ በቀጥተኛ ሽያጭ ኢንዱስትሪ አንጋፋው የስልጠና እና የመሪነት ምሳሌ ኤሊት አምባሳደር ኢንጂነር ታጠቅ ጌታቸው የኢቲኬር መሪነትን ሀ ሁ ሊያስቀስመን በመድረኩ ይገኛል።
እንደሁልጊዜው የቀጥተኛ ሽያጭ ውበት የሆነውን በጋራ መስራት፡በጋር የሚሰሩን መምራት እና አብሮ የመስራትን ስኬቶች ልንቃኝ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ እግሮች ሁሉ ወደ ኢቲኬር ዋና መስሪያ ቤት ያመራሉ።
ነገ ረቡእ ሰኔ 10
ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ
በኢቲኬር ዋና መስሪያ ቤት አዳራሽ
ከኢቲኬር ማስተር አሰልጣኝ ኤሊት አምባሳደር ኢንጂነር ታጠቅ ጌታቸው ጋር
መግቢያ በነጻ
16/06/2026
ትክክለኛ ስጦታዎች ትርጉም እና ምክንያት አላቸው
ትክክለኛውን ስጦታ ከትክክለኛ ምክንያት ጋር እነሆ ከኢቲኬር
ተፈጥሯዊ፣ለሁሉም ቆዳ ተስማሚ ፣ ለውበት ትክክለኛው ምርጫ በኢቲኬር የውበት መጠበቂያ ምርቶች
ያለ ኬሚካል ውህድ ከተፈጥሯዊ እጽዋት ውህድ የተዘጋጁ ውድ ስጦታዎችን ለእራስዎ ለቆዳዎ፣ለጸጉርዎ እንዲሁም ለሚወዱት ሁሉ የሚያበረክቱት ትክክለኛ ምርጫ
Etcare
15/06/2026
ሰኞ እንዲህ አልፏል
በኢቲኬር ሰኞ የሳምንት መጀመሪያ ብቻ ሳይሆን የአእምሮ ዝግጅት በእውቀት
የተግባር ክዋኔ በልምድ የሚታገዝበት ቀን ነው
ሳምንታዊው የኢቲኬር የሕይወት ክህሎት ስልጠና ሰኞን ጠብቆ በኢቲኬር ዋና መስሪያ ቤት ከታላቁ አሰልጣኝ ኤሊት አምባሳደር ማስተር አሰልጣኝ ተመስገን ሀይሉ ጋር ተከናውኗል።
ለሳምንት ብሎም ለዘላቂ ህይወታቸው ክህሎትን ከሽያጭ አቅም ጋር ዲሲፕሊንን ከተግባራዊ ክንውን ጋር ለመቅሰም የተገኙ ኢቲኬሪያንስ ደማቁን የስልጠና መድረክ ይበልጥ አድምቀው ሳምንታቸውን በግሩም የስልጠና ጊዜ ጀምረዋል።
Etcare
15/06/2026
ባህርዳር ዝግጁ?
ኢቲኬር ባህርዳር የደረጃ አሳኪዎች የእውቅና መርሀግብር እና የስልጠና ድግስ
ከጣና ሀይቅ ዳር ደማቅ ስኬትን የተቀዳጁ ኢቲኬሪያንስን በጉልህ በአደባባይ የምንሞሽርበት ታላቅ ድግስ ሊከወን ነው።
ታላላቅ የኢቲኬር መሪዎችን ከፊት አድርጎ ቀዳሚዎቹን አሸናፊዎች ለ ስኬታቸው እውቅና ለስራቸው ምስጋና ለሚደርሱበት ህልም ደግሞ ስንቅ ለማስያዝ ይሆን ዘንድ
እሁድ ሰኔ 14 ኢቲኬር ባህርዳር ደማቅ መሰናዶ አዘጋጅቷል።
በዚህ በአይነቱ ልዩ በሆነው ዝግጅት ላይ በመገኘት ለስኬት ምስክር ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል።
እሁድ ሰኔ 14
በአማራ ስቴት ዩኒቨርስቲ ባህርዳር
14/06/2026
ሰኞ ደርሷል!
ሳምንታችንን በግሩም እውቀት የምንጀምርበት የስልጠና ድግስ እንደተለመደው ነገ በታላቅ ድምቀት ይከናወናል።
የህይወት ክህሎት እና ቀጥተኛ ሽያጭ ከልምድ እና ተሞክሮ ጋር በኢቲኬር ማስተር አሰልጣኝ ኤሊት አምባሳደር ተመስገን ሀይሉ
ነገ ሰኞ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ
በኢቲኬር ዋና መስሪያ ቤት አዳራሽ
መግቢያ በነጻ
ሳምንትዎን 1 ብለው የሚጀምሩበትን የስልጠና ድግስ መካፈልዎን እርግጠኛ ይሁኑ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Https://maps. App. Goo. Gl/9awY8x3TpHfJixMi 9
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:00 - 07:00 |
| Tuesday | 08:00 - 13:00 |
| Wednesday | 08:00 - 13:00 |
| Friday | 08:00 - 13:00 |
| Sunday | 08:00 - 13:00 |
