Brand Fitness Machines

Brand Fitness Machines

Share

ዘመናዊ ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን ከኛ ያገኛሉ። 0953012345 ላይ ይደውሉልን።

15/07/2026

ከባድ ፑሽ አፕ መስራት ከፈለጋችሁ ማድረግ የምትችሏቸው 5 ነገሮች

1. እግራችሁን ከፍ ያለ ነገር ላይ ሰቅላችሁ መስራት
2. የምትሰሩትን ዙር እና ድግግሞሽ መጨመር
3. በፍጥነት ብዙ ከምትሰሩ ቀስ ብላችሁ ትንሽ መስራት
4. ክብደት ጨምራችሁ መስራት
5. በየመሃሉ የምታርፉትን ሰአት መቀነስ

እናንተ ሳታርፉ ስንት ፑሽ አፕ ትሰራላችሁ? ኮሜንት ያድርጉልን።

ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡

14/07/2026

አዲስ ብረት ገፊዎች ለውጥ ለማየት ምን ያህል ጊዜ የሚፈጅባችሁ ይመስላችኋል?

1. የመጀመሪያዎቹ 4 ሳምንታት ላይ የምታዩት የጥንካሬ ለውጥ በጡንቻ እድገት ምክንያት የሚመጣ ሳይሆን በነርቭ ስርአት ለውጥ ምክንያት ነው። ይህም ሰውነታችሁ ውጤታማ በሆነ መንገድ ጡንቻዎችን ማዘዝ መጀመሩን ያሳያል።

2. በሰውነታችሁ ላይ ለውጥ የምታዩት ከሁለት እስከ ሶስት ወር ከሰራችሁ በኋላ ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ የጡንቻችሁ መጠን እየጨመረ እና እያደገ ይሄዳል።

3. ከ4 እስከ 6 ወር ወጥ በሆነ መልኩ ከሰራችሁ ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የጡንቻ እድገት እና ጥንካሬ ይኖራችኋል ።

ጡንቻ በመገንባት ሂደት ውስጥ ዋናው ነገር ወጥ የሆነ አሰራር ፣ ጥሩ አመጋገብ መከተል እና በደንብ እረፍት መውሰድ ነው።

እናንተ ለውጥ ለማየት ምን ያህል ጊዜ ፈጀባችሁ? ኮሜንት ያደርጉልን።

ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡

13/07/2026

ስፖርት ሳታሟሙቁ ስትሰሩ በሰውነታችሁ ላይ ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል?

1. ባልተፍታቱ እና ባልተዘጋጁ ጡንቻዎች ላይ ስፖርት ስትሰሩ ለጡንቻ ፣ ለጅማት እና ለመገጣጠሚያ ጉዳት ያጋልጣችኋል።
2. ማሟሟቅ የደም ዝውውርን በመጨመር ጡንቻ ለስፖርት እንዲዘጋጅ ያግዘዋል። ይህን አለማድረግ የምትሰሩት ስፖርት በምትፈልጉት መጠን ፍሬ እንዳያፈራ ያደርገዋል።
3. ከፍተኛ ለሆነ የስትራፖ ህመም ያጋልጣችኋል።
4. ብዙ ሳትሰሩ በቀላሉ እንዲደክማችሁ ያደርጋል።
5. ባልተሟሟቀ ሰውነት ላይ ከባድ ስፖርት ስትሰሩ የልብ ምታችሁን ያዛባዋል።

እናንተ ለምን ያህል ደቂቃ ታሟሙቃላችሁ? ኮሜንት ያደርጉልን።

ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡

12/07/2026

የእግር ስፖርት አለመስራት በቴስቴስትሮናችሁ ላይ የሚፈጥረው ጫና ምን ይመስላችኋል?

የእግር ስፖርት ስትሰሩ ከፍተኛ መጠን ያለው ቴስቴስትሮን ይለቀቃል። ይህም እጅ ወይም ደረትን ስታሰሩ ከሚለቀቀው በእጥፍ ይበልጣል።

ቴስቴስትሮን ጡንቻን በከፍተኛ መጠን ከማሳደጉ በተጨማሪ ከጉዳት በፍጥነት እንድታገግሙ ያግዛል። በተቃራኒው የእግር የማትሰሩ ከሆነ በሰውነታችሁ ውስጥ የሚለቀቀው ቴስቴስትሮን አነስተኛ ነው። ስለዚህ የእግር ስፖርት ብትሰሩ ይመረጣል።
እናንተ በሳምንት ያህል ጊዜ የእግር ስፖርት ትሰራላችሁ? ኮሜንት ያደርጉልን።

ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡

11/07/2026

ብረት ስትገፉ ወገባችሁን የሚያማችሁ ለምን ይመስላችኋል?

አቋማችሁ ትክክል እንዳልሆነ እና የብረት አነሳሳችሁ የተሳሳተ እንደሆነ ያሳያል። ወገባችሁን እያመማችሁ ብረት ማንሳት ለዲስክ መንሸራተት እና ለጡንቻ ጉዳት ያጋልጣችኋል።

በተለይ ዴድ ሊፊት እና ስኳት ስትሰሩ ትክክለኛ አቋም ወይም ፎርም ይዛችሁ የማትሰሩ ከሆነ መሰል ችግሮች ይከሰታሉ። ይህንን ለመከላከል በቅድሚያ ማሟሟቅ እና ማሳሳብ ይኖርባችኋል። ከዛ በተጨማሪ የሚያሰራችሁ ሰው ከሌለ ዴድሊፍት ባትሰሩ ይመረጣል። ህመሙ እየባሰ ወይም እየቀጠለ ከሄደ ግን የህክምና ባለሙያ ብታማክሩ የተሻለ ነው።
እናንተ ብረት ስትገፉ ወገባችሁን ያማችኋል? ኮሜንት ያድርጉልን።

ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡

10/07/2026

በቤት ውስጥ መስራት የምትችሏቸው ሁለት የትራይሴፕስ ስፖርቶች

1. Diamond Pushup
• ዳይመንድ ፑሽ አፕ ስትሰሩ የእጃችሁ አቀማመጥ የተቀራረብ ስለሚሆን ትራይሴፕስን ለማሰራት ተመረጭ ያደርገዋል። ከዛ በተጨማሪ ደረትን እና ትከሻን በማሰራት የላይኛው የሰውነት ክፍል ጥንካሬ እንዲጨምር ያደርጋል።

2. Bench Dips
• ይህ ስፖርት የትራይሴፕስን መጠን እና ጥንካሬ ለመጨመር ያግዛል። ከመጠን በላይ እየወረዳችሁ ስትሰሩት በትከሻ ላይ ውጥረት ስለሚፈጥር እስከ ግማሽ ድረስ እየወረዳችሁ መስራት ይኖርባችኋል። የተሻለ ውጤት ለማግኘት እንቅስቃሴያችሁን ተቆጣጥራችሁ በእርጋታ ብትሰሩት ይመረጣል።
እናንተ በቤታችሁ የምትሰሩት ስፖርት ምንድነው? ኮሜንት ያደርጉልን።

ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡

09/07/2026

ስፖርት ከመጀመራችሁ በፊት ለምን ያህል ደቂቃ ማሟሟቅ ያለባችሁ ይመስላችኋል?

ከስፖርት በፊት ማሟሟቅ ጡንቻዎችን በማፍታታት እና የደም ዝውውርን በመጨመር የምትሰሩት ስፖርት ውጤታማ እንዲሆን ያደርገዋል። ከዛ በተጨማሪ መገጣጠሚያዎችን እና ጅማቶችን በማፍታታት ብረት በትክክል እንድትገፉ ያደርጋችኋል።

1. ስለዚህ ከባድ የጥንካሬ ስፖርቶችን የምትሰሩ ከሆነ ከ10 - 15 ደቂቃ ማሟሟቅ ይኖርባችኋል ።
2. ቀለል ያሉ ስፖርቶች የምትሰሩ ከሆነ ከ 5-10 ደቂቃ በቂ ነው።

እናንተ ከስፖርት በፊት ለምን ያህል ደቂቃ ታሟሙቃላችሁ? ኮሜንት ያድርጉልን።

ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡

08/07/2026

ከባድ የስትራፖ ህመም እንዳይዛችሁ ማድረግ የምትችሏቸው 4 ነገሮች

1. ውሃ በደንብ መጠጣት
• ከስፖርት በፊትና በኋላ እንዲሁም ስፖርት ስትሰሩ ውሃ በደንብ መጠጣት አላስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን ለማስወገድ ያግዛል።

2. እረፍት መውሰድ
• በደንብ መተኛት እና ማረፍ ጡንቻዎች እራሳቸውን እንዲጠገኑ እና እንዲያድጉ ያደርጋቸዋል።

3. ማማሟቅና ማቀዝቀዝ
• እነዚህ ጡንቻዎችን በማፍታታት እና የደም ዝውውርን በመጨመር የጩንቻ ህመምን ለማስታገስ ያግዛሉ።

4. መራመድና መዋኘት
• እነዚህ የደም ዝውውርን በመጨመር ፣ ምግብና አክስጅን ለጡንቻ በማቅረብ የጡንቻ ህመምን ለማስታገስ ይረዳሉ።

የስትራፖ ህመም የሚያስቸግራችሁ ለምን ያህል ቀን ነው? ኮሜንት ያድርጉልን።

ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Addis Ababa