Fati Ahmadin
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Fati Ahmadin, Health/Beauty, Dire, Addis Ababa.
05/07/2026
05/07/2026
05/07/2026
በክልሉ የሕግ የበላይነት ለማረጋገጥና የመንግስትና የህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ውጤታማ ስራ ተከናውናል
በክልሉ የሕግ የበላይነት ለማረጋገጥና የመንግስትና የህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል።
የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ አዩብ አህመድ በበጀት አመቱ በተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትና የተገኙ ስኬቶች በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በበጀት አመቱ በክልሉ የህዝብና የመንግሥትን ጥቅም ለማስጠበቅ እና ቀልጣፋና ዘመናዊ አሰራርን በመዘርጋት የፍትህ ሥርዓትን ውጤታማነት ለማጎልበት በትኩረት ሲሰራ ቆይቷል።
የተለያዩ ወንጀሎችን በማጣራት አጥፊዎችን በፍርድ ቤት ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን ጠቁመው በክልል ደረጃ የወንጀል መዝገብ የማስቀጣት ምጠኔ 95% ላይ ከማድረስ በተጨማሪ በክልሉ CRIMS የሚባል ዘመናዊ የወንጀል ምርመራ እና ምዝገባ ስርዓት እውን ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
ለዚህም በክልሉ ሙስናን ጨምሮ የተፈፀሙ የተለያዩ ወንጀሎችን በማጣራት 1,389 በሚሆኑ መዝገቦች ላይ የወንጀል ክስ ለፍ/ቤት በማቅረብ አጥፊዎች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን ገልጸዋል።
በበጀት አመቱ መንግስት ሊያጣው የነበረን 21 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ለመንግሰት ገቢ እንዲሆን መደረጉን ጠቁመዋል።
ቢሮው በክልሉና ከክልሉ ውጪ ባሉ ፍ/ቤቶች መንግስትን በመወከል በ40 የፍትሐ ብሔር መዝገቦች ላይ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ የህግና ማስረጃ ክርክር በማድረግ የህግ ጥበቃ እንዲኖረው ተደርጓል ብለዋል።
ከተለያዩ አካላት ጋር በፍትሐ ብሔር ጉዳይ ላይ በመደራደር 81 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የመንግስትና የህዝብ ጥቅም እንዲጠበቅ ስለመደረጉም አብራርተዋል።
በክልሉ ህገወጥ የሰነድ ዝግጅትን ለመከላከል እና ቀልጣፋ አገልግሎት ከመስጠት አንፃርም 14 ሺህ 353 ሰነዶችን የማረጋገጥ ስራ መከናወኑንም ተናግረዋል።
በቀጣይም የህግ የበላይነት ለማረጋገጥና የመንግስትና የህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ በላቀ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።
04/07/2026
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Dire
Addis Ababa
