Caltu abdii
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Caltu abdii, Health/Beauty, Addis Ababa.
01/10/2026
የጽንፈኛዉ ቡድን አፈቀላጤዎች ህዝባዊ ተቀባይነትን አጥተዋል
ጽንፈኛው የህወሃት ቡድን ከትናትናዉ ስህተቶቹ ሳይማር ዛሬም ከሻዕቢያና ግብጽ ጋር ተባብሮ እናት ሃገሩን በመዉጋት ላይ ይገኛል።
ቡድኑ ጽምዶ የሚባል ጥምረት በመፍጠር ቀጣናዉን የትርምስና የጦርነት ማዕከል ለማድረግ እያደገ ያለዉ እንቅስቃሴ በመላዉ ኢትዮጵያዊያንና በአለም አቀፍ ተቋማት ጭምር እየተወገዘ ይገኛል።
የክልሉ ተወላጆች፤ ምሁራን፤ ፖለቲከኞችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ህገወጥ ቡድኑ እያደረገ ያለውን የጦርነት እንቅስቃሴ ሲያወግዙ መቆየታቸዉም የሚታወስ ነዉ።
ህገወጥ ቡድኑ የሻዕቢያና የግብጽ ተላላኪ መሆኑን ሳያዉቁ በተለያዩ መንገዶች አብረዉት ጦርነት ሲቀሰቅሱ የነበሩ አንዳንድ አክቲቪስቶች፤ ፖለቲከኞችና ዳያስፓራዎች ዛሬ ላይ የጦርነት እንቅስቃሴዉን በተለያዩ መንገዶች በመቃወምና በማዉገዝ ላይ ይገኛሉ፡፡
ህገ ወጥ ቡድኑ ከሻዕቢያና ከግብጽ ጋር የፈጠረዉ ጥምረት የኢትዮጵያን ህልዉና የሚገዳደርና ሃገር አፍራሽ መሆኑን ነዉ ታዋቂ የቡድኑ አፈቀላጤዎች እየተናገሩ የሚገኙት።
ጽንፈኛ ሃይሎቹ የግብጽን የጥፋት ተልዕኮ ከማስፈጸም በስተቀር ከኢትዮጵያ ጋር የሚዋጉበት ምንም ተጨባጭ ምክንያትም ሆነ ሥነ ልቦና የላቸዉም።
ኢትዮጵያ ግን በግብጽ ሴራ በተደጋጋሚ ተወግታለች: የባህር በሯን አጥታለች: በባህር በር እጦት ምክንያት ለኢኮኖሚ ጫና ከመጋለጧም በላይ የጂኦግራፊ እስረኛ ሆናለች ይላሉ የህወሃት ታዋቂ አፈቀላጤዎች።
ከዚህ በተቃራኒዉ ግን ስለ ትግራይ ህዝብ ሰላምና ልማት የማይጨነቁ አንዳንድ የቡድኑ አፈቀላጤዎች ዛሬም ለግል ጥቅማቸዉ ብለዉ የትግራይ ወጣቶችን ለጦርነት ከማነሳሳትና ከመቀስቀስ አልፈዉ የጽምዶን ሃገር የማፍረስ ሙከራ እያበረታቱ ይገኛሉ፡፡
እነዚህ የህገ- ወጥ ቡድኑ የዲጂታል ሚዲያ ሰራዊቶች በተደራጀ መንገድ ጦርነት ይቀሰቅሳሉ፤ ጥላቻን ያባዛሉ፤ ሃሰተኛና የተዛቡ መረጃዎችን ያሰራጫሉ፡፡
ያልተደረገዉን ተደርጓል: የተደረገዉን አልደተረገም በማለት በመንታ ምላሳቸዉ ህዝብን ግራ ለማጋባት ይታትራሉ።
በአማራና አፋር ክልሎች ተደጋጋሚ ጦርነቶችን የከፈተዉና ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናገድ የሚሯሯጠዉ ራሱ ህገ ወጥ ቡድኑ መሆኑን እያወቁ የህልዉና አደጋ ተጋርጦብናል ብለዉ በፈጠራ ወሬ ህዝቡን ለማደናገር ይሞክራሉ።
በትግራይ ክልል ከሚፈጠሩ ጦርነቶች ጀርባ ሆነዉ ህዝቡን ለጦርነት የሚቀሰቅሱት የዲጂታል ሚዲያ ሰራዊቶቹ እስከ ዛሬ ድረስ የትግራይ ክልልን ሰላምና ልማት ከማደናቀፍ ዉጪ ለህዝቡ ያመጡት አንዳችም ለውጥ የለም፡፡
አፈ ቀላጤዎቹ በግብጽ ድጋፍ አዲስ አበባን ጨምሮ በሃገር ዉስጥና በዉጭ ሃገራት የተንደላቀቀ ኑሮ እየኖሩ የትግራይ ወጣቶች በክልላቸዉ ሰላማዊ ህይወት እንዳኖሩ፤ ከገዛ ክልላቸዉ እንዲፈናቀሉ፤ የጦርነትና የስደት ሰለባ እንዲሆኑ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
የህወሃት ተቀላቢ አክቲቪስቶቹ ወጣቶችን ለጦርነት፤ ለግጭትና ለስደት ከማነሳሳት ዉጪ እነሱ ትናንትም ሆነ ዛሬ አይሞቱም፤ አይቆስሉም፤ አይራቡም፤ አይሰደዱም፡፡
አፈቀላጤዎቹ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ከኢትዮጵያዊነት ባህል፤ ሃይማኖት፤ ወግና ስርዓት ያፈነገጡና ብሄርና ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ አጸያፊ ቃላትን በመጠቀምና በወንድማማች ህዝቦች መካከል ጸብ በመዝራት ይታወቃሉ።
ጽንፈኞቹ ከጀግናዉ የሃገር መከላከያ ሠራዊትና ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የመገዳደር ሥነ ልቦናና አቅም ሳይኖራቸዉ ራሳቸዉን ሃያልና ጠንካራ አድርገዉ ህዝብን ለማደናገር ይሞክራሉ።
ሃሰተኛና የበሬ ወለደ መረጃዎችን በመፈብረክ ህዝብን በማሸበር የሚታወቁት የህገ ወጡ የህወሃት ቡድንና የጽምዶ አፈቀላጤዎች ዛሬም ህገ ወጡ ቡድኑ በሥነ ልቦናና በዉጊያ አቅም መሸነፉንና መፍረሱን እያወቁ ህዝብንና አለምን ለማደናገር ይሞክራሉ።
ከግብጽ ጋር ባላቸዉ ጠንካራ የጥቅም ትስስር ለአንዳንድ አለም አቀፍ ጋዜጠኞች: ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች የተሳሳቱ መረጃዎችን በመስጠት ዛሬም እንደ ትናንቱ በመቃብር አፋፍ ላይ የቆመዉን ህወሃትን ማጀገንና የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ ለማጠልሸት ይሞክራሉ።
መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ህገ ወጥ ቡድኑ ህዝባዊ ተቀባይነትን ከማጣት: በሥነ ልቦናና በወታደራዊ አቅም ከመፈራረሱም በላይ ለረጅም አመታት ያደራጀዉና ሃሰተኛ መረጃዎችን በመፈብረክ የሚታወቀዉ የዲጂታል ሚዲያ ክንፍ በህዝብና በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነትን አጥቷል። ጽምዶንም ከመሸነፍና ከመፍረስ መታደግ አልቻለም።
01/10/2026
01/10/2026
01/10/2026
01/10/2026
01/10/2026
የኢትዮጵያ የትግል ስልት ተለውጧል፤ የእኛ የትግል ስልት ዛሬ ሰርተን ነገን መዋጀት ነው!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Category
Website
Address
Addis Ababa
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when Caltu abdii posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.
