Aariif Jemal Harar

Aariif Jemal Harar

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Aariif Jemal Harar, Health/Beauty, Harar, Addis Ababa.

07/07/2026

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

የፓርላማ ቆይታችንን ተከትሎ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አከናውነናል። በዚህ የአረንጓዴ ዐሻራ ወቅት ተስፋን መትከላችንን እንቀጥላለን!

07/07/2026

የዘንድሮ ምርጫ ለየትኛውም የፖለቲካ አካል እጅግ አስተማሪና የኢትዮጵያን ህዝብ ጥልቅ አሳቢነትና ሰላም ወዳድነት በትልቁ ያሳየ ትልቅ ታሪካዊ ሁነት ሆኖ ተመዝግቧል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

07/07/2026

የዘንድሮው ምርጫ ለመማር ፈቃደኛ ለሆነ ሁሉ ትምህርት የሰጠ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር)

07/07/2026

በ6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሰጡት ማብራሪያ።

⨳7ተኛው ጠቅላላ ምርጫን በሚመለከት

- ማሸነፍ ከፈተና መሻገር ፈተናዎችን በብልሃት የማለፍ ልምድ ያለው ህዝብ እንዳለን ያየንበት ነው።

- በዘንድሮ ምርጫ ማድረግ አትችሉም፣አይሳካም የሚሉ ፅንፈኞች ቢኖሩም፤ኢትዮጵያውያን ግን በአንድ ድምፅ አሳክተነዋል።

-ፅንፈኝነት አያስፈልገንም፤ባንዳነትም አያስፈልገንም!

-አዛውንቶች ወጥተው ድምፅ የሰጡት ልጆቻችን ሀገር እና ሀገረ መንግስት ያስፈልጋቸዋል ብለው ነው።

-በኢትዮጵያ ህዝብ የምርጫ ታሪክ፣ በአፍሪካ ሕዝብ የምርጫ ታሪክ አድርገው በማያውቁት ልክ አሳክተን አሳይተናል።

07/07/2026

ፕሪቶሪያ እንደ ድርድር ብቻ የሚታይ ሳይሆን ብዙ ውጤት የተገኘበት የሰላም ስምምነት ነው። ከሁሉም በላይ አሸናፊ እና ተሸናፊ እኩል ቁጭ ብለው የተወያዩበት ድርድር ሲሆን መንግሥት ካሸነፈ በኋላ ከተሸናፊ ኃይል ጋር መደራደር መቻሉን አሳይቷል። መንግሥት መደራደር ብቻም ሳይሆን በችግር ውስጥ ለሚገኙ የታጠቁ ኃይሎች በርካታ ድጋፍ በማድረግ ሰላምን ለማጽናት ያለውን ቁርጠኝነት ማሳየት ችሏል፡፡

ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

07/07/2026

ሀገራዊ ምክክርን በተመለከተ

“ይህንን ሰፊ ሀገራዊ እድል በመጠቀም፣ ካለፉት እሰጥ አገባዎች ወጥተን በሰለጠነ መንገድ መወያየት ይኖርብናል። በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ያሉትን አወንታዊ እሴቶች ይዘን እንቀጥል፤ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸውን ነጥቦች ደግሞ ማንንም በማይጎዳ፣ የሁሉንም መብት በሚያከብርና አንድነታችንን በሚያጠናክር መልኩ እናሻሽላለን።ዋናው መገንዘብ ያለብን ነጥብ፦ አሁን የምንመክረው የአንድን ጊዜያዊ ገዥ ፓርቲ ስህተት ለማረም ብቻ አይደለም። ይልቁኑ ለዘመናት የተከማቹ ስር የሰደዱ ሀገራዊ ችግሮቻችንን በጋራ ጠረጴዛ ዙሪያ ፈትተን፣ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የሚበጅ አዲስ ማህበራዊ ውል ለመፈረም ነው። ይህ ምክክር በመወያየት፣ በመነጋገርና በመተማመን እንዴት አብሮ መኖር ይቻላል ለሚለው ታሪካዊ ጥያቄ ዘላቂ ምላሽ የምንሰጥበት ብቸኛው መንገድ ነው!”

07/07/2026
07/07/2026

የትምህርት ዘርፍ ጥራት እና ለውጦችን በተመለከተ፦

የትምህርት ዘርፍ ጥራትን ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ ለውጥ እየመጣ ነው። ባለፉት ዓመታት ተማሪዎች በራሳቸው ተማምነው ፈተና የሚወስዱበት አሰራር ተተግብሯል፤ በዚህም የኩራጃ ባህልን ማስረቀት ተችሏል። ትምህርት ከታች ካልተሠራ ከላይ መሥራት ውጤታማ አያደርግም፤ ለመዋዕለ ህጻናት ማስፋፊያ በተሰጠው ትኩረት 35 ሺህ መዋዕለ ሕጻናትን መገንባት ተችሏል። የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ኩረጃን ለማስቀረት፣ ትምህርትን በቴክኖሎጂ ለማስፋፋት እየተደረገ ያለው ሙከራ ተስፋ ሰጪ ነው። የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም ደረጃቸውን የጠበቁ እጅግ አበረታች ግንባታዎች እየተከናወኑ ይገኛል።

07/07/2026

ግብርና እና የምግብ ሉዓላዊነትን በተመለከተ፦

በዘንድሮው የምርት ዘመን 29 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማረስ 1.3 ቢሊዮን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉ እንዲሁም ዘርፉ የ7.7 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡ፤ የኢትዮጵያ ግብርና እያሳየ ላለው መዋቅራዊ ሽግግር ግልጽ ማሳያ ነው። በሀገር አቀፍ ደረጃ የተተገበረው የ‘ሌማት ትሩፋት’ መርሃ-ግብር አስደናቂ ውጤቶችን ያስመዘገበ ሲሆን፣ በተለይም አቮካዶን ወደ ውጭ በመላክ ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃን መያዝ መቻሉ ለሀገሪቱ ተጨማሪ ከፍተኛ ገቢ በማስገኘት አስደናቂ ድል እንዲመዘገብ አስችሏል። ከዚህም በላይ ለረጅም ጊዜ በከባድ ድርቅ ይጎዳ የነበረው የቦረና ቀጣና ዛሬ በሰፊ የስንዴ ልማት ተሸፍኖ ማየት መቻሉ የስትራቴጂያዊ ግብርና ስራችንን ስኬታማነት ያረጋግጣል። ምንም እንኳ የዓለም አቀፍ ጫናዎች ቢበዙም፣ የማዳበሪያ እና የነዳጅ ዋጋ ቢንርም፣ በቁርጠኝነትና በጠንካራ ስራ በምግብ ራሳችንን ለመቻልና በአፍሪካ ላይ የተለጠፈውን የረሃብ ታሪክ ለመቀየር በተግባር እየሰራን እንገኛለን፤ ምክንያቱም ምርጫችን ለምኖ መኖር ሳይሆን ሰርቶ ማደር ነው!

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Harar
Addis Ababa