Chaltu hailu
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Chaltu hailu, Health/Beauty, Addis Ababa.
20/05/2026
23/04/2026
ዛሬ ጠዋት የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (Africa CDC) ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ከዶክተር ዣን ካሴያ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገናል። በውይይታችን በተለያዩ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ የመከርን ሲሆን፤ በተለይም በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) በመሆን የተሰጠኝን አዲስ ኃላፊነት በሚመለከት በስፋት ተነጋግረናል።
የፈጠራ ሥራዎች ለአፍሪካ ዕድገት ምንጊዜም ወሳኝ መሰረት ናቸው። በጤናው ዘርፍ የሚገጥመንን ተለዋዋጭ ተግዳሮቶች ለመወጣት የሰው ሰራሽ አስተውሎትንና የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ዐቅም መጠቀም የጤና ሥርዓታችንን ለማጠናከር፣ ተደራሽነትን ለማስፋፋት እና ለሕዝባችን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ወሳኝ ነው። ኢትዮጵያ ያላትን ልምድ ለአህጉሩ ለማካፈል እንዲሁም በፍጥነት ከሚለዋወጠው የቴክኖሎጂው ዓለም ጋር ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመራመድ የሚያስችሉ ጠንካራ አጋርነቶችን ለመመሥረት ያላትን ቁርጠኝነት ዳግም ታረጋግጣለች።
ይህንን ርዕይ ወደ ተጨባጭና አካታች ውጤት ለመለወጥ ከአፍሪካ ሲዲሲ (Africa CDC) እና በመላው አህጉሪቱ ከሚገኙ አጋሮች ጋር በቅርበት ለመሥራት ዝግጁ ነኝ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ(ዶ/ር)
17/03/2026
ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ የሀዘን መግለጫ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ላካ ቀበሌ መጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ በዜጎቻችን ላይ በደረሰው የህይወት መጥፋትና መፈናቀል የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል።
በዚህ አሰቃቂ አደጋ የ52 ወገኖቻችን ህይወት ማለፉ የተረጋገጠ ሲሆን፣ መንግሥት ለሟች ቤተሰቦች፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለጋሞ ዞን እና ለመላው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ልባዊ መጽናናትን ይመኛል።
በአሁኑ ወቅት የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በአደጋው ስፍራ በመገኘት የተጎዱ ወገኖችን የማጽናናትና የድጋፍ ስራዎችን በቅርበት እየተከታተሉ የሚገኙ ሲሆን በአደጋው ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ቁሳቁሶችና የምግብ አቅርቦት በአስቸኳይ እንዲደርስ ክልሉ ከፌዴራል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት ሰፊ የርብርብ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል ።
መንግሥት ጊዜያዊ ድጋፍ በማድረግ ብቻ ሳይወሰን፣ ተጎጂዎችን ወደ ቀደመ ኑሯቸው ለመመለስና በዘላቂነት ለማቋቋም ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ ሲሆን ተጨማሪ የህይወትና የንብረት ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከልም የስጋት ቀጠና ተብለው በተለዩ ስፍራዎች የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የማንሳትና ወደ አስተማማኝ አካባቢዎች የማዘዋወር ሥራ በቅንጅትና በትኩረት እየተከናወነ ይገኛል።
በአሁኑ ወቅት ያለው ዝናባማ የአየር ሁኔታ መሰል አደጋዎችን ሊያስከትል ስለሚችል፣ በተለይም በደጋማና ለናዳ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ከመንግሥት የሚሰጡ የጥንቃቄ መልዕክቶችንና መመሪያዎችን በአንክሮ በመተግበር አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል ።
የኢፌዴሪ መንግሥት በአደጋው ሳቢያ የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ከክልሉ መንግሥትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራቱን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፤ ለሟች ወገኖቻችን ሰላማዊ እረፍትን፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን ይመኛል ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa
