Amlaku Gebeyehu
teacher
01/04/2026
01/04/2026
መልካም ቀን የልባችንን መሻት ያሞላልን
19/02/2026
ቸር ቀን
14/02/2026
ተመስገን መልካም ቅበላ
05/08/2022
03/08/2022
03/08/2022
03/07/2022
ከምግብ በኋላ ፈፅሞ የማይመከሩ ነገሮች
1. ሻይ አይጠጡ
ሻይ በሰውነታችን ከፍተኛ መጠን ያለው አሲድ እንዳይፈጠር ያደርጋል፡፡ ይህ አሲድም በተመገብነው ምግብ ውስጥ ያሉ ፕሮቲኖች እንዲጠነክሩ አልፈጭ እንዲሉ ያደርጋቸዋል፡፡
2. አያጭሱ
ምግብ ከተመገቡ በኋላ ወዲያው ሲጋራ ማጨስ አደገኛ ነው ከምግብ በኋላ የሚያጨሱ ሰዎች በሣንባ ካንሰር የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ነወ፡፡
3. ፍራፍሬ አይመገቡ ከምግብ በኋላ ወዲያውኑ ፍራፍሬ መመገብ አንጀታችን ወዲያውኑ በአየር እንዲወጣጠር ያደርገዋል፡፡ፍራፍሬ መብላት ከፈለጉ፤ምግብ ከመመግብዎ ከአንድ ሰአት በፊት ወይም ከተመገብዎ ከአንድ ሰአት ተኩል በኋላ ቢሆን ይመረጣል፡፡
4. ገላዎን አይታጠቡ ምግብ ከተመገቡ በኋላ ወዲያውኑ ገላን መታጠብ በእግርና በጃችን አካባቢ የደም ፍሰት (ዝውውር) መጠኑ እንዲጨምር የሚያደርግ ሲሆን በሆዳችን ያለው አካባቢ የደም ፍሰት ይቀንሰዋል፡፡በዚም ምክንያት የምግብ ስልቀጣ ይዳከማል፡፡
5. ቀዝቃዛ ውሃ አይጠጡ ከምግብ በኋላ ቀዝቃዛ ውሃ ከበላነው ምግብ ውሰጥ የሚገኙት ዘይት ነክ ነገሮች ወደ ጠጣርነት ይቀየራቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ የምግብ መፍጨት ከመጓተቱም በላይ ወደ ጠጣርነት የቀየረውን ዘይት እና ቅባት ጨጓራ ውስጥ የሚገኝ አሲድ ጋር በማገናኘት በፍጥነት ተሰባብሮ ወደ አንጀት ውስጥ እንዲገባ ያደርገዋል፡፡ይህም ወደ ስብነት ተቀይሮ ለካንሰር ሰበብ መጋለጥ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን ከምግብ በኋላ ቀዝቃዛ ውሃ ከመጠጣት ይቆጠቡ፡፡ በምትኩ ለብ ያለ ውኃ መጠጣት የምግብ ልመት ስርአጡ የተሳካ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡
6.የእግር ጉዞ አያድርጉ ከምግብ በኋላ ወዲያውኑ የእግር ጉውዞ ማድረግ የምግብ ስልጠቃ ሂደት በአግባቡ እንዳይከናወን ያደርገዋል፡፡
7. ወዲያውኑ አይተኙ በልተን ወዲያውኑ ከተኛን የተመገብነው ምግብ በአግባቡ አይፈጭም፡፡ ይህ ደግሞ ለጨጓራ ህመምን ለአንጀት ቁስለት ይዳርጋል፡፡
ጤናና ሰላም ከናንተ ጋር ይሁን
ምንጭ:- ጠቅላላ ዕውቀት ጥያቄና መልስ General Knowledge
Health info and vaccancy news
#ሼር በማድረግ ለሌሎችም ያጋሩ 🙏
---------------------------------------------
ተጨማሪ እና ወቅታዊ ቪዲዮዎችን ለማየት ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው የ You tube ቻናላችንን Subscribe በማድረግ አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ 🙏
You tube
⬇️⬇️⬇️
https://youtube.com/channel/UCCdO4NN5iEU0WQfmvzBasGA
01/07/2022
ጠላት አርፎ እንደማይተኛ ታውቆ ለየትኛውም ተጋድሎ ራስን ማዘጋጀት እንደሚገባ የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ።
ባሕር ዳር: ሰኔ 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ግዛቸው ሙሉነህ በውቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም የአማራ ክልል የፀጥታ ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ተወያይቶ አቅጣጫ ማስቀመጡን ገልፀዋል። ውስጣዊ አንድነትን ለማጠናከር እና የውጭ ጠላትን ለመመከት የሕግ ማስከበር ሥራ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል። የሕግ ማስከበር ሥራው ውጤት የታየበት መሆኑን የፀጥታ ምክር ቤቱ መገምገሙንና ጉድለቶችንም መመልከቱን ነው የተናገሩት።
እየተወሰደ ባለው የሕግ ማስከበር ሥራ ክልሉ ወደ ሰላም መምጣቱንም አንስተዋል። የሽብር ቡድኖች ዋነኛ ዓላማ ሕዝብ መንግሥትን እንዲጠራጠር ማድረግ እንደነበርም ገልጸዋል። ጠላት የአማራ ክልል የትርምስ ቀጣና የማድረግ ዓላማ ይዞ እየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል። የፀጥታ ምክር ቤቱ የጠላትን እንቅስቃሴ መገምገሙንም አስታውቀዋል። የአማራ ክልል በተፈናቃዮች እንዲሞላ ጠላት እንደሚሠራም ገልጸዋል። ጠላት ዜጎችን በግፍ ከመግደል ባለፈ በልዩ ልዩ ሰበቦች ሁከትና ብጥብጥ የመፍጠር ተግባር ለመሥራት እየጣረ መሆኑንም ገልጸዋል።
በዜጎች ላይ በደረሰው ጉዳት የክልሉ መንግሥት ማዘኑን የገለፁት አቶ ግዛቸው ጠላት አሁንም ለሌላ ብጥብጥ ጉዳዮን ለመጠቀም እየሠራ ነው ብለዋል። የውጭ ጠላቶች ላይ አተኩሮ መሥራት ይገባልም ነው ያሉት። የውስጥ አንድነት እስከሌለ ድረስ ለጠላት እንጋለጣለን ያሉት ኃላፊው በብስለትና ኃይል በማሰባሰብ በጠላት ላይ በጋራ መዝመት እንደሚገባ ነው የገለጹት። ከኋላ የሚወጋ ኃይል እንዳይኖር የውስጥ ጠላትን እያፅዱ ከውጭ ጠላት ጋር መታገል ይገባል ነው ያሉት።
የክልሉ ሕዝብና መንግሥት ለሰላም የቆመ ነው ያሉት አቶ ግዛቸው ሕግና ሥርዓት የማስከበር ሥራ የአንድ ሠሞን ሳይሆን ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የፀጥታ ምክር ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል ብለዋል።
አሸባሪዎችን መልክ ለማስያዝና አንኳር ጥያቄዎች እንዲመለሱ ሕግና ሥርዓት መከበር እንዳለበትም አስታውቀዋል።
የፀጥታ ምክር ቤቱ አሁናዊ የውጭ ጠላቶችን እንቅስቃሴ በመገምገም አቅጣጫ አስቀምጧልም ብለዋል። ክረምቱን መነሻ በማድረግ የጠላት እንቅስቃሴ መኖሩንም ገልጸዋል። የጠላትን እንቅስቃሴ ለመመከትም በሁሉም ዘርፍ መዘጋጀት እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል ነው ያሉት። የፖለቲካ ሁኔታው በሚገባ መሥራት እንዳለበት መግባባት ላይ መደረሱንም ገልጸዋል። ለሕዝቡ መረጃን ቶሎ ቶሎ ማድረስ እንደሚገባም አቅጣጫ ተቀምጧል ነው ያሉት።
ዜጎችን በሚጨፈጭፉ የሽብር ቡድኖች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑንም አንስተዋል። የዜጎችን መጨፍጨፍ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በአማራ ክልል የበለጠ ብጥብጥ ለመፍጠር የሚጥሩ ጠላቶች መኖራቸውንም ገልጸዋል። ጠላት አርፎ እንደማይተኛ ታውቆ ለየትኛውም ተጋድሎ ራስን ማዘጋጀት እንደሚገባ የፀጥታ ምክር ቤቱ አቅጣጫ ማስቀመጡን አንስተዋል። ጠላት የሚፈራውና የሚያከብረው የፀጥታ ኃይል መገንባት ይገባልም ነው ያሉት። ሕዝቡ ለፀጥታ ኃይሉ አስተማማኝ ደጀን ሆኖ ለሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች አጋዥ እንዲሆንም አሳስበዋል።
ከፀጥታው ጎን ለጎን የልማት ሥራዎች መሠራት እንደሚገባም ተናግረዋል። ጠላቶች በወሳኝ ወቅት በአማራ ክልል የልማት ሥራዎች እንዳይሰሩና ክልሉ ከድህነት እንዳይወጣ የማድረግ ሥራ እንደሚሠሩም አንስተዋል። የኑሮ ውድነትን ለመፍታት የልማት ሥራዎችን በትኩረት መሥራት ይገባል ነው ያሉት።
ሕግ የማስከበር ሥራው ጠላቶች እንደሚሉት አማራን የማዳከም ሳይሆን አማራን የማጠናከር መሆኑንም አስገንዝበዋል። ሕዝቡም የሕግ ማስከበር ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየጠየቀ መሆኑንም ገልጸዋል። ለአማራ ሕዝብ ጥቅምና አንድነት የቆመን አካል የመያዝ ዓላማ እንደሌለ አስታውቀዋል። ሕግን ባከበረ መልኩ ሕግ የማስከበር ሥራው መቀጠል እንደሚገባውም የፀጥታ ምክር ቤቱ በአፅንኦት እንደገመገመው ነው የተናገሩት።
የአማራና የኦሮሚያ ክልል መንግሥታት የጥፋት ተልዕኮዎችን በጋራ ለማጥፋት እየሠሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል። ኦነግ ሸኔን ለማጥፋት የፀጥታ ኃይሎች በቅንጅት እየሠሩ መሆናቸውንም አንስተዋል። ጠላቶች ዜጎችን እየጨፈጨፉ የአማራን ሕዝብ ማስቆጣትና ሌላ ብጥብጥ እንዲያነሳ እንደሚፈልጉ የተናገሩት አቶ ግዛቸው ሕዝቡ የጠላትን አሰላለፍ መረዳት እንደሚገባው ነው የተናገሩት። የዜጎች ጭፍጨፋ ያስቆጣል፣ ያሳስባልም፣ መፍትሔው ግን በትግል ሥልቱ መግባባት እና መደራጀት ይገባል ነው ያሉት።
አሸባሪውና ወራሪው ትህነግ ለጦርነት ሲዝት እንደኖረና አሁንም እየዛተ እንደሆነ የተናገሩት አቶ ግዛቸው የአማራ ሕዝብ የሰው አይነካም የራሱንም አሳልፎ አይሰጥም፣ ይሄን አቋማችን አጠናክረን እንቀጥላለን፣ ለሰላም ቅድሚያ እንሰጣለን ከዚያ በላይ ለሚመጣ ጉዳይ ዝግጅት ያስፈልጋል፣ ክልሉ የሚጠበቅበትን ያደርጋል ነው ያሉት። ክልሉ ከሌሎች ክልሎች ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑንም አስታወቀዋል። በመከፋፈል እና ጠላት በሚፈጥረው አጀንዳ በመራመድ ጥያቄዎችን ማስመለስ፣ ሰላምም ማምጣት አይቻልም ነው ያሉት። የጠላት ኃይል እስካልከሰመ ድረስ የዜጎች ሞት ሊቀርና ሰላም ሊመጣ እንደማይችል በመገንዘብ በአንድነት መሥራት ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ:-ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
30/06/2022
ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተሰጠ መግለጫ
*************
(ኢ ፕ ድ)
ጽንፈኛ ኃይሎች ከውስጥና ከውጭ ጠላቶቻችን ጋር በመቀናጀት የሀገሪቱን ሰላምና ደህንነት ለማወክ እየሰሩ መሆኑን ፖሊስ ባገኛቸው መረጃዎች ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አሰታወቀ።
ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተሰጠው መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል።
አለመግባባቶችን ሰበብ በማድረግ ጽንፈኛ ኃይሎች ከውስጥና ከውጭ ጠላቶቻችን ጋር በመቀናጀት የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት ለማወክ እየሰሩ መሆኑን ፖሊስ ባገኛቸው መረጃዎች አረጋግጧል።
በዛሬው ዕለት የተደረጁ ኃይሎች የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ቢሮን መስታወት በመሰባበር መጠነኛ ጉዳት አድርሰዋል።
ፖሊስ እነዚህን ኃይሎች በቁጥጥር ስር አውሎ በህግ አግባብ ተጠያቂ እንዲሆኑ ምርመራ እያጣራባቸው መሆኑን ይገልፃል።
ከዚህ በተጨማሪ ጽንፈኛ ኃይሎች ከውጭ ጠላቶቻችን ጋር ተቀናጅተው የሀገራችንን ጸጥታ ለማደፍረስ የተለያዩ መሣሪያዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ጥረት እያደረጉ እንደሆነ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ስለሆነም መላው የሀገራችን ሙስሊም ህብረተሰብ ይህንን ተገንዝቦ የሀገሩንና የሀይማኖቱን ሰላምና ደህንነት እንዳይደፈርስ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ እያሳሰብን፣ ፖሊስ ከድርግታቸው በማይቆጠቡት ላይ ጥብቅ ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ያሳውቃል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Bahir Dar
