Bahir dar Blood Bank Service
የባሕር ዳር ደም ባንክ አገልግሎት ይምጡ ደም በመለገስ ወገንዎን ይታደጉ
11/07/2026
የ2018 ምርጥ 3ተኛ ደረጃ የደም ማሰባሰብ ተሸላሚ የነበረው የአጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ የክረምት በጎፈቃድን በደም ልገሳ ኘሮግራም አስጀመረ
ሐምሌ 04 ቀን 2018 ዓ.ም በባሕርዳር ከተማ አስተዳደር የአጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ፣ " ደም ያስተሳስረናል" በሚል መሪ ሐሳብ የደም ልገሳ መርሃ ግብር በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል።
መርሃ ግብሩ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አንዱ አካል ሲሆን፣ በበጎ ፈቃደኞችና በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ሰፊ ተሳትፎ ይከናወናል። በመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች ደም በመለገስ ሕይወት የማዳን ሰብዓዊ ተግባራቸውን አሳይተዋል።
የደም ልገሳ ሕይወትን የሚያድን ከፍተኛ ሰብዓዊ ተግባር መሆኑ ተጠቅሶ፣ እንዲህ ያሉ የበጎነት ተግባራት የመረዳዳትና የአብሮነት ባህልን በማጠናከር ጤናማና የተባበረ ማህበረሰብ ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ተገልጿል።
ደም ያስተሳስረናል
11/07/2026
አሜን ልዩ የህክምና ማዕከል የደም ልገሳ ኘሮግራም ተካሄደ!!
ደም ያስተሳስረናል!!
11/07/2026
አንድም እናት በደም እጦት መሞት የለባትም። የፋሲሎ ክፍለ ከተማ የደም ልገሳ ፕሮግራም ሐምሌ 04/2018
ደም ያስተሳስረናል
11/07/2026
ጣና ክፍለ ከተማ የህዳሴ ቀበሌ የደም ልገሳ ፕሮግራም በዚህ መልኩ እየተካሄደ ነው።
“ደሜን ለወገኔ” በሚል መሪ ቃል በክረምት ወራት በተዘጋጀው በዚህ ፕሮግራም ላይ በርካታ የቀበሌው ነዋሪዎችና ወጣቶች በመገኘት ደም በመለገስ ሰብአዊነታቸውን በተግባር እያሳዩ ይገኛሉ።
ይህ ንቅናቄ የወገንን ህይወት ለመታደግና የበጎነት ባህልን ለማሳደግ ታላቅ አስተዋጽኦ ያለው ሲሆን፣ የህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎም ለቀጣይ የበጎ ፍቃድ ስራዎች ስኬት ትልቅ መነሳሳትን ፈጥሯል።
ደም ያስተሳስረናል
11/07/2026
የ2018 ምርጥ 1ኛ የደም ማሰባሰብ ተሸላሚ የነበረው የግሽ ዓባይ ክፍለ ከተማ የክረምት በጎፈቃድን በደም ልገሳ ኘሮግራም አስጀመረ
ሐምሌ 04 ቀን 2018 ዓ.ም በባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ግሽ ዓባይ ክፍለ ከተማ፣ "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሐሳብ የደም ልገሳ መርሃ ግብር በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል።
መርሃ ግብሩ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አንዱ አካል ሲሆን፣ በበጎ ፈቃደኞችና በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ሰፊ ተሳትፎ ይከናወናል። በመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች ደም በመለገስ ሕይወት የማዳን ሰብዓዊ ተግባራቸውን አሳይተዋል።
የደም ልገሳ ሕይወትን የሚያድን ከፍተኛ ሰብዓዊ ተግባር መሆኑ ተጠቅሶ፣ እንዲህ ያሉ የበጎነት ተግባራት የመረዳዳትና የአብሮነት ባህልን በማጠናከር ጤናማና የተባበረ ማህበረሰብ ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ተገልጿል።
ደም ያስተሳስረናል
❤️ አንድ ከረጢት ደም፤ ሙሉ ሕይወት ሊያድን ይችላል!❤
ዛሬ የምትለግሱት ደም ለአደጋ ተጎጂ፣ ለወላድ እናት፣ ለታመመ ሕፃን ወይም በደም ሕክምና እያደረገ ላለ ሰው የሕይወት ተስፋ ሊሆን ይችላል።
ደም በገንዘብ አይገዛም፤ በሰብዓዊነት ብቻ ይሰጣል። ዛሬ ጥቂት ደቂቃዎችን በመስጠት አንድን ሰው ከሞት ልታድኑ ትችላላችሁ።
**"ደም መለገስ ሕይወት መስጠት ነው!"**
❤️🩸
ደም ያስተሳስረናል!!
09/07/2026
የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች በንቅናቄ በደም ልገሳ ስላስጀመራችሁ እናመሰግናለን።
ደም ያስተሳስረናል
09/07/2026
ዶክተር ዓዕምሮ የእናቶችና ህጻናት ህክምና ማዕከል ባለሙያዎችና በጎፈቃደኞች ደም ስለለገሳችሁ እናመሰግናለን።
ደም ያስተሳስረናል!!
08/07/2026
በባህርዳር የዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለከተማ የደም ልገሳ ኘሮግራም በደመቀ ሁኔታ በማስጀመር ከ 40 በላይ ሰዎች ደም እንዲለግሱ ሁኗል!! እናመሰግናለን!!
ሌሎች ክፍለከተማዎች ይቀጥላሉ!
ደም ያስተሳስረናል!!
የ2018 ዓ.ም የዓመቱ ምርጥ አንደኛ ተሸላሚ ትምህርት ቤት
ጣና ሀይቅ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Address
Bahir Dar
Bahir Dar
