Libo kemkem W. Health Promotion

Libo kemkem W.  Health Promotion

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Libo kemkem W. Health Promotion, Health/Beauty, Bahir Dar.

17/03/2023

♨``አትበሳጭ ብስጭት የስይጣን ነውና``
♨ አትዘን '' አምላክ ያልፈቀደው አይሆንምና`
♨`አትቸኩል
``ላንተ ያለው አይቀርምና``✔

✔️ፍቅርማለት በሀብት ብዛትያልታጠረች በድህነት ወስን ያልተገደበች በወርቅ ሚዛንላይ ያልተቀመጠች
በግለስቡ ማንነት ብቻ የምትገለፅ ጥበብ ነች💋💋

✔️አንድ አንዱ ዛሬ የሚያስደስተው ሲያገኝ ትላንት መስዋእት የሆነለትን ይረሳል………………

💍ቃል የእምነት እዳ ነው ❤ፍቅርም ልክ እንደ ማህተም ነው ከቃልም በላይ እውነት እና እምነት ነው፡፡💍
``
✔️ፍቅርማለት በሀብት ብዛትያልታጠረች በድህነት ወስን ያልተገደበች በወርቅ ሚዛንላይ ያልተቀመጠች
በግለስቡ ማንነት ብቻ የምትገለፅ ጥበብ ነች💋💋

✔️ሴት ልጅ የማይቻለውን ነገር አድርግልኝ ብላ አትጠይቅህም ነገር ግን አንት ለእህትህ የምትመኘውን አይነት ወንድ ሁንላት ይሄ ብቻ በቂዋ ነው፡፡

❤️ፍቅር እንኳዋን ርቀት መከራንም ይታግሳል
`

✍ዓለም ሙሉ ጎድቶህ አንድ ስው ሊያስደስትህ ይችላል
©°ያው ሰው አንድ ቀን ይጎዳህና
ዓለም ሙሉ አንተን ማስደስት ያቅተዋል

✍ ከድብቅ ጓደኛ ግልፅ ጠላት ይሻላል✔


✍ወዳጄ ሆይ!
💝ልብህ ለፍቅር
💓ህሊናህን ለእውነት
💟ነብስህን ለፀሎት አድርገው! Firaw//78

ፔጁን ሼር ላይ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ

በውስጥ ለምትሰጡን ገንቢ አስተያየት ከልብ እናመሰግናለን 🌷🌷🌷

ምርጥ ምርጥ አባባሎች
ከደራሲያን አለም ፔጅ
Ethiopia24 News

17/03/2023

#ላሻግርህ 😥 😢
___አስራ ሁለት ሰአት አካባቢ ነዉ። ገብረኤል ቤተክርስቲያንን ተሳልሜ ወደግቢ ለመግባት ዜብራ ልሻገር እግረኛ መንገድ ላይ ቆሜላሁ ።

አጠገቤ አንድ በእይታ ብቻ የማዉቀዉ አይነ ስዉር ልጅ ቆሟል።
ወደ ግቢ እንደሆነ ጠየኩት። አዎ ወደ ግቢ ነኝ አለኝ። እኔም ቆይ ዜብራዉን ላሻግርህ ብዬ በግራ እጁ እኔን ይዞ በቀኝ እጁ ደግሞ ኬኑን /ኬን ማለት አይነ ስዉራን የሚይዙት ተጣጣፊ ዘንግ ነዉ/ አጣጥፎ በአጭሩ ይዟል።

እኔም ፌስብኩ ላይ የሆነ ነገር በትኩረት እያነበብኩ እየተሻገርን ሳለ ድንገት ገጭ የሚል ድምፅ ሰማሁ። ደንግጬ ዘወር ስል ልጁ ከመንገድ ዳር የመብራት ፖል ጋር ተጋጨ እኔም በጣም ደነገጥኩ።

የተመታዉን ቦታ እያሸሁለት " ወ ይ ኔ በጣም ይቅርታ የሆነ ነገር እኮ ፌስቡክ ላይ አይቼ እያነበብኩ ስለነበር ነው.." ብዬ ሳልጨርስ ደስ የሚል ፈገግታ እያሳየኝ
"ችግር የለውም አልመታኝሞ በዛ ላይ ጥፋቱ የእኔ ነው " አለኝ እኔም በጣም ግራ በመጋባት
" እኔ ነኝ እኮ ጥፋተኛው። ላሻግርህ እኮ ነበር እጅህን የያዝኩት ግን...." ብዬ ሳልጨረስ አሁንም ፈገግ እያለ እንደህ አለኝ

በርግጥ ልታሻግረኝ ነበር። ነገር ግን አንተ አይን ሳላለህ እና እኔን ማሻገር ስለምትችል ሁሉን ነገር የምትችል መስሎህ ሁለት ስራ መስራት ፈለክ።
በአይንህ እያነበብክ በእጅህ ደግሞ እኔን ልታሻግር አሰብክ ግን አልተሳካም።
ምክንያቱም መጀመሪያ ለሚብሰዉ/ለከባዱ/ ነገር ቅድሚያ መስጠት ነበረብህ ይህንን ባለማድረግህ ተሳሳትክ

እኔም አንተ ማየት እና ማሻገር ስለምትችል ብቻ እና ና ላሽግርህ ስላልከኝ ብቻ ሙሉ እምነቴን ለአንተ ሰጥቼ ኬኔን/ዘንጌን/ አጣጥፌ መያዝ አልነበረብኝም። ምክንያቱም አንተ አሻጋሪዬ ብትሳሳት ወይም እንደ አሁንህ የሆነ ሀሳብ ዉስጥ ስትገባ ዘንጌን አጣጥፌ ባልይዝ ቢያንስ ፖሉ ሳይመታኝ መዳን እና አንተንም ከችግሩ በፊት ማንቃት እችል ነበር።

ስለዚህ አንተም ላሻግርህ አልከኝ አመንኩህ። እጄን ስትይዘኝ ሀሳብህን በሙሉ እኔን ማሻገር ላይ ማድረግ አለብህ። እኔም አንተም ሆንክ ማንም ና ላሻግርህ ብሎ ስላለኝ ብቻ ሙሉ እምነቴን ለእሱ ሰጥቼ ዘንጌን አጣጥፌ መቀመጥ የለብኝም።
ምክንያቱም የሚያሻግረኝ ሰው ነው በሆነ ነገር ሀሳቡ ሊሰረቅ፣ የሆነ ነገር ቀልቡን ስቦት እኔን ሊያስረሳዉ ይችላል... አለኝ።

በጣም ደነገጥኩ። ነገሩን የተረዳበት እና ያስረዳበት መንገድ በጣም አስደነገጠኝ። መጨረሻ ላይ ተሰነባብተን ወደ ዶርሜ አመራሁ። ግን አንድ ነገር በጆሮዬ አቃጨለብኝ:: " ላሻግርህ ስላልከኝ.... አመንኩህ ግን አጋጨኸኝ.."
ያለኝ እንቅልፍ ነሳኝ 😥😥😥

አ መ ሠ ግ ና ለ ሁ

17/03/2023

ጌታ ሆይ 🙌 እስካሁን የኖርኩት ወጀብና አውሎ ንፋስ ጠፍቶ አልነበረም ፤ ያልታመምኩት በሽታ ሳይኖር ቀርቶ አይደለም፡፡ ጉልበት የሆነኝ የጠበቀኝና የሸፈነኝ ስለ እኔ በቀራኒዮ መስቀል ላይ የፈሰሰው ደምህ ነውና ክብር ምስጋና ለአንተ ይገባል✞ 🙌

Join This Group : የቸርነት Tube

17/03/2023

ጋዜጠኛው ክሪስቲያኖ ሮናልዶን እንዲህ ሲል ጠየቀው:-
ለምንድነው እናትህ አሁንም ከአንተ ጋር የምትኖረው? ለምን የራሷን ቤት አትገዛላትም?’
ክሪስቲያኖ መለሰ:- እናቴ የራሷን ህይወት መስዋዕት አድርጋ ነው እኔን ያሳደገችኝ፡፡ ራቴን በልቼ እንድተኛ ፆሟን ታድር ነበር፡፡ ገንዘብ የሚባል ነገር ጭራሽ አልነበረንም፡፡ የመጀመሪያውን የእግር ኳስ ትጥቄን አሟልቼ እንድጫወት በሳምንት ሰባት ቀን፤ ቀን እና ምሽቱን ጽዳት ሠራተኛ ሆና አሳልፋለች፡፡ የኔ ጠቅላላ ስኬት ለእሷ የተሰጠ ማስታወሻ ነው፡፡ እኔ በህይወት እስካለሁ ሁልጊዜም ከጎኔ ትኖራለች፡፡ ከእኔ ማግኘት ያለባትን ሁሉ እሰጣታለሁ:: መሸሸጊያዬና የህይወቴ ታላቋ በረከት እናቴ ብቻ ናት።

እባኮዎን join ያድርጉ

መልካም ጤንነት ተመኘዎሎ ዶ/ክ ቤዛ አያሌው
Join "Dr beza" on Telegram: https://t.me/httpstmepsFCxwAQEQpjZDA0

17/03/2023
17/03/2023

ከሚፈርዱብን ጋር አብሮ አይፈርድብንም፡፡

ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርሱዋን አቁመው። መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት።

የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤ መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ። ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው። ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ።

እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች። ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት።

እርስዋም ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ አለች። ኢየሱስም እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት ( ዮሐ 8 ፥ 1 - 11 ።

ማብራሪያ

ሴቲቱን ስታመነዝር አገኘናት በማለት ከታላቁ እስከ ታናሹ ይዘዋት መጡ፡፡ ትወገር ባዮቹ የራሳቸው ያልታያቸው ፈራጆችና አስፈራጆች ነበሩ፡፡

የሰውን ኃጢአት በቀራንዮ በመስቀል ላይ ራሱ ተሸክሞ ፣ እንደ ሙሴ ሕግ ይወገሩ የሚለውን ሕግ ሊያስቀር እንደ መጣ አላወቁም፡፡ ደጋግመው ሲጠይቁት ከእናንተ ኃጢአት የሌለባት ይውገራት አላቸው፡፡ እንዳይወግሩአት ደግሞ እነርሱም መውገር የማይችሉ ኃጢአተኞች ነበሩ፡፡ ኃጢአት የሌለበት አንድም ወጋሪ ታጥቶ ሁሉም ጥለዋት ጠፉ፡፡

ስለ ኃጢአቷ ሊሞትላት መጥቶ ትወገር አሉ፡፡ እንደዚህ ያሉትን ሊፈልግና ሊያድን እንደ መጣ አላስተዋሉም፡፡ ስለ እነርሱም ኃጢአት ሳይቀር ሊሞት ነበር የመጣው፡፡ ከሚፈርዱባት ጋር አብሮ ሳይፈርድ ደግመሽ ኃጢአትን አትስሪ በማለት ይቅር ብሎ አሰናበታት፡፡

ዛሬ በኛ ድካም የሌሉ በሌላ ድካም ግን ተይዘው፣ ዛሬ በሚከሱበንም ኃጢአት ጭምር ነገ ሊሰፈሩ እንደሚችሉ ዘንግተው ፈራጅ የሚሆኑ አሉ፡፡ እነርሱ ስላሉ ግን እርሱ በኛ ላይ አይፈርድብንም፤ የመጣው የኛን ኃጢአት በመስቀል ላይ ለመሸከም ነውና፤ የሚፈርዱብን የማያስተውሉት የእነርሱንም ኃጢአት ለመሸም እንደ መጣ ነው፡፡

የሚፈርዱብን የእነርሱን ዘንግተው የእኛ ድካም ቢታያቸውም የእኛንም የእነርሱንም ኃጢአት ሊሸከም በቀራንዮ የተሰቀለው ጌታ የሚፈርዱብንም በደለኞች እንደ ሆኑ አውቆ በኛ ላይ ከእነርሱ ጋር አብሮ አይፈርድብንም፡፡

ቢፈረድማ ኖሮ ሁላችንም ኃጢአተኞች ስለሆንን የሚፈርድብንም ሳይቀር በእውነተኛ ፈራጅ ፊት ይፈረድበት ነበር፡፡ ሊፈርድብን የሚገባው መድኀኔ ዓለም ኃጢአታችንን በቀራንዮ ተሸክሞ ሳለ ማንም በኛ ላይ ሊፈርድብን፣ በማንም ላይ ልንፈርድም አይገባንም፡፡

ወስብሐት ለእግዚብሔር:: አሜን!

ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ሰባኬ ወንጌል ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ

ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን ለመስማት ለምትፈልጉ በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w

ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq

21/10/2022

!
ትልቁ ጀግንነት ➖➖➖ #ትእግስት
ትልቁ ስልጣን ➖➖➖ እራስን መግዛት
ትልቁ ስብእና ➖➖➖ #መልካምነት
ትልቁ ማንነት➖➖➖ ታማኝነት
ትልቁ ድህነት ➖➖➖ #እውቀት ማጣት
ትልቁ ድክመት ➖➖➖ለገንዘብ መገዛት
ትልቁ ስልጣኔ ➖➖➖ #መረዳዳት
ትልቁ በሽታ ➖➖➖ ሁሉንም አውቃለሁ
ትልቁ ስጦታ ➖➖➖ #ፍቅር
ትልቁ ሀብት ➖➖➖እምነት
ትልቁ ጭንቀት ➖➖➖
Nebil Nur

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Bahir Dar?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Bahir Dar
TAMRALECHADGO