Bahar abdi
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bahar abdi, Health/Beauty, Harar.
23/07/2026
23/07/2026
የቁልቢ ገብርኤል በዓለ ንግስ በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት መደረጉን ኮሚሽኑ አስታወቀ
በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የቁልቢ ገብርኤል በዓለ ንግስ በሰላምና በደመቀ መልኩ እንዲከበር ለማስቻል የቅድመ ዝግጅቱን ተግባራት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ነገራ ዱፌራ እንደገለጹት በዓሉ በሰላምና በደመቀ መልኩ እንዲከበር ለማስቻል ለሁሉም ፈፃሚ አመራር እና አባላት እንዲሁም አጋዥ ተቋማት የበዓሉን አከባበር የተመለከተ የፀጥታ እቅድ ወቶ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ከማድረግ ጀምሮ ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል።
አሁን ወቅትም የበዓሉ አከባበር በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊ የሰው ኃይል ተመድቦ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።
ከበዓሉ ጋር ተያይዞ ወደ ከተማው የሚመጡ እንግዶች እና ነዋሪው አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ወድያውኑ ለፖሊስ ጥቆማ መስጠት ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ምክትል ኮሚሽነር ነገራ አያይዘውም ሊደርሱ የሚችሉ የትራፊክ አደጋዎች ለመከላከል መላ አሽከርካሪዎች በትእግስት እና የመንገድ አጠቃቀም ህግና ስርዓትን ባከበረ መልኩ ማሽከርከር ይገባቸዋል ብለዋል።
ምክትል ኮሚሽነሩ ባስተላለፉት መልዕክት ሰላም ወዳዱ የክልሉ ሕዝብ እንደ ወትሮው ሁሉ ከፖሊስና ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በጋራ እንዲሰራ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
23/07/2026
በሀረሪ ክልል ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች ነፃ የጤና ምርመራና ህክምና እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ
በሀረሪ ክልል ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች ነፃ የጤና ምርመራና ህክምና አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።
የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አካል የሆነው ነፃ የህክምና አገልግሎት "በጎነት ለጤናማ ማህበረሰብ" በሚል ሀሳብ ነው እየተሰጠ የሚገኝው።
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አብዲ አሚን እንደገለጹት እየተሰጠ የሚገኝው ነፃ የምርመራና የህክምና አገልግሎት አቅመ ደካማ ለሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።
ነፃ የህክምና አገልግሎቱ በበጎ ፍቃደኛ የጤና ባለሙያዎች አማካኝነት እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመው አገልግሎቱም በመንግስትና በተመረጡ የግል ጤና ተቋማት እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።
እየተሰጡ ከሚገኙ የጤና ምርመራዎች መካከልም የስኳር ህመም፣ የደም ግፊት፣ ከአንገት በላይ፣ የቆዳና የአይን እና የልብ ሕመም ምርመራና ሕክምና እንዲሁም ሌሎች ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ይገኙበታል ብለዋል ከዚህ በተጨማሪም ከ5 ሺህ በላይ የደም ልገሳ መርሃ ግብሮች እንደሚካሄድ ገልጸዋል።
በምርመራው ወቅትም ተጨማሪ ህክምና ምርመራ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ወደ ሚመለከታቸው የጤና ተቋማት በመላክ አገልግሎቱን እንዲያገኙ እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት።
ከዚህ በተጨማሪም በዘመቻው ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን አስመልክቶ ለሕብረተሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።
ዘመቻው የጤና አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ የህዝብን የጤና ንቃት ለማሳደግና የመረዳዳት ባህልን ለማሳደግ የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል።
በመሆኑም ኅብረተሰቡ ይህንን በመገንዘብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
23/07/2026
22/07/2026
"ማረሚያ ቤቱ ታራሚዎችን በሙያና ስነ ምግባር በማነፅ ብቁ ዜጎች የሚፈጠሩበት እንዲሆን ትኩረት መሰጠቱን የሀረሪ ክልል ማረሚያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አድናን አህመድ ገለፁ።
ኮሚሽነሩ የኮሚሽኑን የቀጣይ ግዜ አቅጣጫ በማስመልከት በሰጡት መግለጫ የታራሚዎችን ሰብዓዊ መብት በመጠበቅ የተመዘገበውን ውጤት በ 2019 ለማጎልበት ይሰራል ብለዋል።
በተለይ ታራሚዎችን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች እንዲሰለጥኑ በማስቻል የተመዘገበውን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚሰራ ነው የገለፁት።
ታራሚዎች በማረሚያ ቆይታቸው የባህሪ ለውጥ እንዲያመጡ በማስቻል ወንጀልን የሚፀየፉ ዜጎች እንዲሆኑ ለማስቻል በትኩረት ይሰራል።
ኮሚሽኑ ታራሚዎች የእርምት ግዜያቸውን አጠናቀው ከማህበረሰቡ ጋር በሚቀላቀሉበት ግዜ በሰለጠኑበት የሙያ ዘርፍ በመሰማራት ሰላማዊና አምራች ሀይል በመሆን ገበያውን እንዲቀላቀሉ ማስቻል አላማው አድርጎ እየሰራ ነው።
በዚህም የማረሚያ ቤቱን የማረም ማነጽ ስርዓት ይበልጥ በማሻሻል ታራሚዎች በስነ ምግባርና ሙያ ታንፀው እንዲወጡ ለማስቻል ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ሲሉ ገልፀዋል።
ታራሚዎችን ገበያ ላይ በሚፈለጉ የሙያ ዘርፎች ይበልጥ ለማብቃት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ኮሚሽኑ ከክልሉ ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር የጀመረው የወረቀት አልባ ሶፍትዌር የማበልጸግ ሥራ በያዝነው የበጀት ዓመት እንዲጠናቀቅ በማድረግ ዘመናዊ፣ ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ያስችላል ብለዋል።
ማረሚያ ኮሚሽኑ የሕግ ታራሚዎችን የማረምና ማነጽ ስርዓቱን ይበልጥ በማሻሻል የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ኮሚሽነር አድናን አህመድ የገለፁት።
22/07/2026
ልማትና ዴሞክራሲን ጎን ለጎን በማስኬድ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በተሰሩ ዘርፈ ብዙ ተግባራት የላቀ ውጤት ተመዝግቧል፡፡ -
አቶ አደም ፋራህ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የብልፅግና ፓርቲ የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Harar
