Sami Mentamo
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sami Mentamo, Health/Beauty, Hosanna.
23/09/2026
የአሜሪካ አምባሳደር #ህወሓት «ሰፊ ጥቃት» መሰንዘሩ « እንዳሳዘናቸው» ገለጹ፤ ችግሩም በውይይት እንዲፈታ ጥሪ አቀረቡ
አዲስ አበባ ፣መስከረም 13 ቀን 2019- በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ፣ የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራሮች «ሰፊ ጥቃት» ለማካሄድ የወሰዱትን ውሳኔ በመቃወም ጥልቅ «ቅሬታ እና ሃዘን» እንደተሰማቸው ገለጹ።
ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በትግራይ እንዲሁም በጎረቤት አፋር እና አማራ ክልሎች አዲስ ግጭት ማገርሸቱ ተዘግቧል።
አምባሳደር ኤርቪን አሜሪካ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ በህወሓት አመራሮች ላይ ማዕቀብ መጣሏን በማስታወስ፣ አመራሮቹ ወደ ወታደራዊ እርምጃ ለመመለስ የወሰኑት ውሳኔ «የተሳሳተ አካሄድ» መሆኑን ጠቁመዋል።
«አሜሪካ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ማዕቀብ የጣለችባቸው የህወሓት አመራሮች ዛሬ ሰፊ ጥቃት ለማካሄድ የተሳሳተ ውሳኔ ሲወስዱ ማየቴ አበሳጭቶኛል» ብለዋል።
የዛሬ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት የትግራይ ኃይሎች የመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያን በቁጥጥር ሥር ያዋሉ ሲሆን፣ በአፋር ክልል አባላ እና እረብቲ አካባቢዎች ከፌደራል ኃይሎች ጋር ተጋጭተዋል።
የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ፣ አክሱም እና ሽሬ አየር ማረፊያዎች የሚያደርጋቸውን የበረራ አገልግሎቶች አግዷል።
አምባሳደሩ አክለውም በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ የሚመራውን የአፍሪካ ህብረት የሰላም ውይይት «ወደ ጎን ማለት» በግጭቱ ለተጎዱ ዜጎች ምንም የሚያስገኘው ጥቅም እንደሌለ አሳስበዋል።
«በፕሬዝዳንት ኦባሳንጆ የሚመራውን የአፍሪካ ህብረት ውይይት ውድቅ ማድረግ እና ማሸነፍ የማይቻል ውጊያ ውስጥ መግባት ለህዝቡ ምንም የሚያስገኘው ጥቅም የለም» ያሉት አምባሳደሩ፣ «ሌሎች ታጣቂ ቡድኖችም ከዚህ አይነት አካሄድ ቢቆጠቡ ብልህነት ነው» ሲሉ አሳስበዋል።
23/09/2026
19/09/2026
14/09/2026
ሩሲያ በዩክሬን እና በፖላንድ ድንበር አቅራቢያ በመንገደኞች ባቡር ላይ የድሮን ጥቃት ፈፀመች። የድሮን ጥቃቱ የተፈፀመው የቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እና ከፍተኛ የአውሮፓ ኅብረት የደኅንነት ባለሥልጣናት በባቡር መስመሩ አልፈው ብዙ ሳይቆይ ነበር። ቦሪስ ጆንሰን እና የዩኬውን ጆናታን ፖዌልን ጨምሮ ሌሎች የአውሮፓ ብሔራዊ የደኅንነት አማካሪዎች በኪየቭ ዓመታዊውን እና መሪዎች፣ የፖለቲካ፣ የቢዝነስ፣ የደኅንነት እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣናት የሚሳተፉበትን ስብሰባ ታድመው ሲመለሱ በሌላ ባቡር በተመሳሳይ የባቡር መንገድ ነበር ያለፉት።
06/09/2026
ታዋቂዋ የግብፅ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ ሳራ ኻሊፋ እና ሌሎች 11 ሰዎች ከአደንዛዥ ዕፅ እና ከሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ጋር በተያያዙ ወንጀሎች ጥፋተኛ ተብለው በስቅላት እንዲቀጡ ተፈረደባቸው።
05/09/2026
🌼"እንቁጣጣሽ "🌻
🌻🌼🌼🌻
🎤 ድምጻዊ ፦ ሙሉጌታ ሱጋሞ (ሙለር ሶንግ)
✍️ ግጥም ፦ መምህር አንድነት ተስፋሁን እና አየነው ታረቀኝ(ባይክ)
🎼 ዜማ ፦ ሙሉጌታ ሱጋሞ እና ቦማንዛ(ቦማንዛ ስቱዲዮ)
🎹 ሙዚቃ ቅንብር ፦ ቦማንዛ (ቦማንዛ ስቱዲዮ)
🎧 ሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ፦ ቦማንዛ(ቦማንዛ ስቱዲዮ)
👨💻 ግራፊክ ፦ አስፋው ዳንኤል
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Hosanna
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when Sami Mentamo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.
