Druggist
We talking About drugstore
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የዜጎችን ጤና እና ደህንነት የመጠበቅ ሕጋዊ ኃላፊነቱን መነሻ በማድረግ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጋር በቅንጅት በሠራው ጥብቅ ክትትል፤ በሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ግዙፍ መጋዘኖች ውስጥ ተከማችቶ የተገኘ ከ13,000 (አስራ ሦስት ሺህ) ኩንታል በላይ ደረጃውን ያልጠበቀ የምግብ ጨው በቁጥጥር ሥር ውሏል።
ባለሥልጣኑ በቁጥጥር ሥር ከዋለው ምርት ላይ ተገቢውን ናሙና በመውሰድ ባከናወነው የላብራቶሪ ምርመራ፤ ምርቱ ለሰው ልጅ ምግብነት እንዲውል ከተቀመጠው ሀገራዊ ደረጃ በታች መሆኑ ተረጋግጧል።
በዚህም መሠረት፦የላብራቶሪ ምርመራ ዉጤቱ እንደሚያሳየዉ
• ምርቱ በአግባቡ ያልተጣራ (Unrefined) በመሆኑ፣ በውስጡ ለጤና ጎጂ ቆሻሻዎችና ኬሚካሎች ከሚፈቀደው መጠን በላይ ተገኝተውበታል።
• በምርቱ ውስጥ ሊኖር የሚገባው የአዮዲን መጠን በደረጃዉ መሰረት ያለመሆኑ ታይቷል ።
• በመሆኑም ይህ ከደረጃ በታች የሆነ ምርት ወደ ማህበረሰቡ እንዳይሰራጭ የታገደ ሲሆን፣ ምርቱን ያሰራጩ ተቋማት ላይ አስፈላጊው እርምጃዎች ተወስደዋል።
የምግብ ጨው ለሰው ልጅ ዕለታዊ የአመጋገብ ስርዓት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው ምርት ነው። በተለይም የአዮዲን እጥረት በህብረተሰቡ ላይ የሚያስከትለውን ከፍተኛ የጤና መታወክ (የአእምሮ እድገት መገታት እና ሌሎች የጤና እክሎች) ለመከላከል ሲባል ጨው በአዮዲን እንዲበለጽግ ይደረጋል። ይህንኑ አስፈላጊነት በማጤን መንግሥት በደንብ ቁጥር 204/2003 መሠረት ማንኛውም ለምግብነት የሚቀርብ ጨው በደረጃው መሠረት በአዮዲን የበለጸገ እንዲሆን ግዴታ ጥሏል።
በምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 መሠረት፣ ማንኛውም በምግብ ማምረት፣ ማከማቸትና ማከፋፈል ሥራ ላይ የተሰማራ አካል፦
• የሚያመርተው ምርት ለጤና ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን የማረጋገጥ፤
• ምርቱ የተቀመጠለትን የጥራት ደረጃ ማሟላቱን የመቆጣጠር፤
• የመልካም አመራረት, አከመቻቸት ስርጭት ስርዓቶችን (GMP፣GSP GDP) በመተግበር የምርቱን ደህንነት የማረጋገጥ ሃላፊነት አለበት።
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን፣ የህብረተሰቡን ጤና አደጋ ላይ በሚጥሉ ሕገ-ወጥ ድርጊቶች ላይ የክትትልና የቁጥጥር ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን እናስታውቃለን። ህብረተሰቡም መሰል አጠራጣሪ ምርቶችንና ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት በባለሥልጣኑ ነጻ ስልክ መስመር 8482 በመደወል ጥቆማ በመስጠት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
የኢትዮጵያ ምግብ መድኃኒት ባለሥልጣን
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
18/12/2025
Hydrocephalus
14/11/2025
08/10/2025
02/10/2025
proton pump inhibitors
22/09/2025
hypertension
👉ስለ ሾተላይ (Rh-isoimmunization) ማወቅ ያለብን ነጥቦች⚠️
በዶ/ር ዳዊት መስፍን ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት
💥 ሾተላይ የሚባለው በሽታ ከሁለተኛ ጀምሮ የሚወለዱ ህፃናትን የሚያጠቃ በሽታ ሲሆን ይህም በእናትና በፅንሱ መሀከል የደም አይነት አለመጣጣም(Rh incompatability) ምክንያት የሚከሰት ነው።
💥 ሾተላይ የሚከሰተዉ የሴቲቱ የደም አይነት Rh negative ፣ የባል የደም አይነት Rh positive እና የፅንሱ ደግሞ Rh positive ከሆነ ሲሆን በተጨማሪም በተለያዩ ምክንያቶች Rh positive ደም ወደ ሴቲቱ ደም ከገባ ወይም ከወሰደች ነው።
🌟 ነጥብ
💥 ሚስት Rh negative መሆን ይኖርባታል እና ፅንሱ Rh positive መሆን ይኖርበታል
💥 ባል Rh negative ከሆነ ሾተላይ አይከሰትም
🌟 ሾተላይ ለምን ይከሰታል?
👉 የሰው ልጅ ከወላጆቹ ዘረመል ተነስቶ ከ4 የደም አይነቶች ውስጥ አንዱን ሊይዝ ይችላል። እነኝህም
1. “A”
2. “B”
3. “AB”
4. “O” ተብለው ይጠራሉ።
👉 በሰውነት ውስጥ የሚገኙ ቀይ የደም ህዋሶች(RBCs) የላይኛው ሽፋናቸው ላይ Rh የተባለ ፕሮቲን (protein) ካላቸው ሴቲቱ Rh positive ናት ማለት ሲሆን እነኚህ ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ Rh negative ናት ማለት ነው።
ለምሳሌ:- ሴቲቱ የደም አይነቷ B ቢሆንና ቀይ የደም ሴሎቿ ላይ Rh ፕሮቲን ካለ B Positive ናት ማለት ነው፤ እነኚህ Rh ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ B Negative ናት ይባላል።
👉 አንዲት ሴት ሾተላይ የሚባለው ችግር ሊከሰትባት የሚችለው እሷ Rh negative ሆና በተለያዩ አጋጣሚዎች Rh positive የሆነ ደም ወደሰውነቷ ሲገባ ሰውነቷ እነኚህን Rh positive የደም አይነቶች የሚያጠፉ(የሚገሉ) ንጥረ ነገሮች (Antibodies) ሲያመነጭ (ሲያመርት) ነው። እነኚህም እስከ እድሜልክ በሰውነቷ ይቆያሉ።
👉 እነኚህ የተመረቱት ተከላካይ ንጥረ ነገሮች(Antibodies) የመጀመሪያው ልጅ ላይ ምንም ተፅዓኖ ሳይኖራቸው ልጁ በሰላም ሊወለድ ይችላል ነገር ግን የሁለተኛው ፅንስ የደም አይነቱ Rh positive ከሆነ ወደ ፅንሱ በማለፍ የፅንሱን Rh positive የቀይ የደም ህዋሶች ያጠቃሉ ማለት ነው፤ ይህም ፅንሱን ለተለያየ አደጋዎች ሊያጋልጠው ይችላል።
👉 ይህም ችግር ፅንሱ ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን ሊያመጣ ይችላል ፤ እነኚህም
☘️ በፅንሱ የተለያዩ የአካል ክፍሎች ውሀ መቋጠር - Fetal hydrops
☘️ በተደጋጋሚ የፅንስ መውረድ - Miscarriage
☘️ የፅንሱ የደም ማነስ - Fetal anemia
☘️ ፅንሱ በማህፀን ውስጥ እንዳለ ጊዜው ሳይደርስ ህይወቱ ማለፍ
☘️ ህፃኑ ከተወለደ በውሃላ ቆዳው ቢጫ መሆን እና የጨረር ህክምና ማስፈለግ(phototherapy)
☘️ በከፍተኛ ደም ማነስ ምክንያት ደም ለመውሰድ መጋለጥ
🌟 ሾተላይ እንዴት ይታከማል?
👉 Rh negative የሆነችው እናት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ነገሮች ከገጠሟት
☘️ ባለቤቷ Rh positive ከሆነ
☘️ ውርጃ ካጋጠማት
☘️ ከማህፀን ውጭ እርግዝና ካጋጠማት
☘️ ከእንግዴ ልጅ ላይ የሚነሳ እጢ(Gestation trophoblastic disease) ካጋጠማት
☘️ በእርግዝና ወቅት አደጋ ከደረሰባት፤
☘️ በክትትል ወቅት ከእንግዴ ልጅ ወይም ከሽርት ዉሃ በመሳሪያ ናሙና ከተወሰደ
👉👉 Anti D የተባለ ኢሚውኖግሎቡሊን (immunoglobulin) መድሀኒት በመውሰድ ሾተላይን መከላከል ይቻላል።
በእርግዝና ጊዜ Anti D የተባለውን መድሃኒትን በ 7 ወር(28 ሳምንት) ላይ እና ህፃኑ በተወለደ ቢቻል እስከ 72 ሰዓት ውስጥ በመስጠት የሾተላይ በሽታን መከላከል ይቻላል።
👉 Rh negative የሆነች እናት(ባል Rh positive) የእርግዝና ክትትሏ ከሌሎች እናቶች ለየት ያለ እና የሚሰጣትም ቀጠሮ በዛ ያለ ይሆናል።
👉 ይህም በልጇ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉትን የሰውነት ውሀ መቋጠር(መጠራቀም) እና የፅንሱ ደም ማነስ ካለ ቀድሞ በማወቅ ህክምናውን በቶሎ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ እዛው ማህፀን ውስጥ እንዳለ ደም በመለገስ እና ወቶ ለመኖር ብቁ በሆነበት ጊዜ ቀድሞ እንዲወለድ በማድረግ ተጨማሪ የሆኑ የህክምና እርዳታዎች እንዲደረግለት ማድረግ ይቻላል።
07/11/2024
Information for safety
amazing heart rate status Just watch
your heart pumps blood
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Shashemene
0000
